Sunday, 02 January 2022 20:40

የRh (አር ኤች) አለመጣጣም፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 የRh (አር ኤች) አለመጣጣም ሲባል ምን ማለት ነው? የሚል ጥያቄ ከብዙዎች ዘንድ የሚነሳ ነው፡፡ Healthline የተባለ ድረ ገጽ ይህንን ርእሰ ጉዳይ በስፋት በመዘርዘር ለንባብ አቅርቦታል፡፡
አንዲት እናትና ያረገዘችው ልጅ በደማቸው ውስጥ የተለያየ የ Rh ፐሮቲን ሲኖራቸው የ Rh አለመጣጣም ይፈጠራል፡፡ ይህም ማለት የእናትየው የደም አይነት Rh-negative ሆኖ የተረ ገዘው ልጅ ደግሞ የደም አይነቱ Rh-positive ሲሆን ነው፡፡ Rh የሚባለው በቀይ የደም ሴል ውስጥ የሚኖረው ፕሮቲን ነው፡፡ እንደየደም አይነቱ የRhየደም አይነት ከወላጆች የሚወረስ ነው፡፡ አብዛኛው ሰው Rh-positive ሲሆን አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ደግሞ Rh-negative ናቸው፡፡ ይህም ማለት የ Rh ፐሮቲን ይጎድላቸዋል ማለት ነው፡፡
Stanford Blood Center የተባለው ማእከል እንዳወጣው መረጃ በደም አይነቶች ውስጥ ኔጌቲቭ እና ፖዘቲቭ የሚኖረው መጠን እንደሚከተለው ተጠቅሶል፡፡ Rh-positive ወይንም ደግሞ Rh-negative በየደም አይነቶቹ አለ፡፡
O+   37.4%       O– 6.6%
A+   35.7%       A– 6.3%
B+    8.5%     B– 1.5%
AB+  3.4%  
ከላይ እንደተመለከተው ሁሉም የደም አይነቶች ኔጌቲቭ እና ፖዘቲቭ በሚል የሚለዩ ሲሆን መጠናቸው ግን የፖዘቲቭ ከፍ ያለ የኔጌቲቭ ደግሞ ዝቅ ያለ መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡
አንዲት እናት የደረሰባቸውን ችግር ሲገልጹ እንዲህ ነበር ያሉት፡፡ እኔ በእድሜዬ ወደ 75/ሰባ አምስት አመት ተጠግቶኛል፡፡ ታዲያ በጊዜው የእርግዝና ምርመራ ሲደረግልኝ አር ኤች ኔጌቲቭ ስለሆንሽ እንደወለድሽ የሚሰጥሽ መድሀኒት ያስፈልግሻል፡፡ ምክንያቱም የመጀመሪያው ልጅ በተለያዩ ህክምናዎች ሊረዳ የሚችል ሲሆን ለሚቀጥለው ልጅ ግን ችግር ስለሚያ ስከትል ነው ተብዬ ነበር፡፡ ታድያ በጊዜው መድሀኒቱን በአገር ውስጥ ማግኘት አልተቻለም፡፡ ቤተሰቦቼ አቅም ስለነበራቸው መድሀ ኒቱን እንደምንም ብለው ከኬንያ በውድ ገንዘብ ተገዝቶ መጣ እና ፍሪጅ ተቀመጠ፡፡ ከዚያም ምጥ የመጣ እለት ያልታሰበ እና እጅግ አስደንጋጭ ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ እኔ የደም ግፊቴ በጣም ከፍ ብሎ ስለ ነበር ምጡን ትቼ እራሴን ስቼ ስወድቅ ህይወቴን ለማዳን ሁሉም በየፊናው ተሯሯጠ፡፡ የሚያሳ ዝነው ነገር የተወለደው ልጅም ከማህጸን ወጥቶ ምንም ያህል ሳይቆይ ህይወቱን ማጣቱን ነው የተነገረኝ፡፡ የእኔን ሕይወት ለማትረፍ በነበረው መጨናነቅ ስለ አር ኤች ኔጌቲቭ ማንም ያስታ ወሰ አልነበረም፡፡ ያስታወሰ ቢኖርም እንኩዋን ለህጻኑ እንጂ ለእኔ የሚሰጥ ስላልመሰላቸው ችላ ብለውታል፡፡በቃ፡ያረገዝኩትን ልጅ ከማጣቴ የበለጠ ድጋሚ ልጅ መውለድ አለመቻሌ ሀዘኔን አበረታው፡፡ ሾተላይ ነች እየተባልኩ ኖርኩ፡፡ ዛሬ እንኩዋን መድሀኒቱ በአገር ውስጥም ስላለ ሴቶቹ እንደማይቸገሩ አምናለሁ፡፡
ወ/ሮ ዝማም በልሁ ከአዲስ አበበ
አር ኤች በእርግዝና ጊዜ የሚያስከትለው ችግር ምንድው?
አንዲት እርጉዝ የሆነች ሴት የእርግዝና ክትትል በምታደርግበት ጊዜ በመጀመሪያ ደረጃ የሚለየው የደም አይነትዋ ምን አይነት እንደሆነ ነው፡፡ በህክምና ካርድዋ ላይ በግልጽ ይቀመጣል፡፡ አንዲት እናት የደምዋ ፖዘቲቭ ወይንም ኔጌቲቭ መሆኑ በቀጥታ በእራስዋ ጤንነት ላይ የሚያስከትለው የጤና ችግር የለም፡፡ ይሁን እንጂ በእርግዝና ወቅት ትኩረትን የሚሻ የምርመራ አካል ነው፡፡ ለምሳሌም እናትየው ደምዋ Rh-negative ከሆነ እና የልጅዋ ደም ደግሞ Rh-positive ከሆነ የእናትየው ሰውነት አንድ እንግዳ ነገር እንደመጣበት ይቆጥ ረዋል፡፡ ይህም ማለት የእናትየው ሰውነት በእርግዝናው ፤በምጥ እና በወሊድ ወቅት ያንን እንግዳ ነገር የሚቋቋም ወይንም ከልጁ ቀይ የደም ሴል በተቃራኒው መከላከያውን antibodies ያዘጋጃል፡፡ antibodies የሰውነት የመቋቋም አቅም የሚፈጥረው መከላከያ ሲሆን እንደ እንግዳ የሚቆጠረ ውን ወይንም ከውጭ የሚገጥምን ችግር ለመቋቋም የሚረዳ ነው፡፡
አንዲት ሴት የደም አይነትዋ Rh-negative ቢሆን Rh-positive የሆነውን ደም ለመቀበል የምትቸገር በመሆኑ ሰውነትዋ መከላከያውን ወይንም antibodies ይፈጥራል ማለት ሰውነትዋ የተፈጠረውን መከላከያ antibodies ወደ እንግዴ ልጅ በመላክ የተረገዘውን ልጅ የቀይ የደም ሴል ለማጥቃት ዝግጁ ይሆናል፡፡ እንግዴ ልጅ ማለት እናትየውንና የተረገዘውን ልጅ የሚያ ገናኝ አካል ነው፡፡
የአር ኤች አለመጣጣምን የሚያሳዩ ምልክቶች ምንድናቸው?
የአር ኤች አለመጣጣም በእርግዝና ላይ ባለው ልጅ ላይ ከመጠነኛ እስከ ከባድ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ችግር አለው፡፡ በእርጉዝዋ እናት ሰውነት አማካኝነት የሚፈጠረው መከ ላከያ anti- bodies የተረገዘውን ህጻን የቀይ የደም ሴል በሚያጠቃበት ጊዜ በቀይ ደም ሴል ስር ላይ ሕመም ሊከሰት ይችላል፡፡ የተረገዘው ልጅ ጤናማ ቀይ የደም ሴሎች በሚጠቁበት ጊዜ በዚያ ምክንያት የሚከሰቱት bilirubin የተሰኙ ኬሚካሎች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ bilirubin ማለት ቀይ የደም ሴሎች በ antibodies እንዲወገዱ በመደረጉ ምክንያት ጉበት በትክክል ስራውን እንዳይ ሰራ በመደረጉ የሚፈጠር ኬሚካል ነው፡፡ የተረገዘው ልጅ bilirubin መጠኑ ከፍ ያለ ከሆነ ከተወለደ በሁዋላ የሚከተሉት ምልክቶች ይኖሩታል፡፡  
Jaundice     (ጁዋንዲስ) ቆዳንና አይንን ብጫ ማድረግ፤
Lethargy      ድካም…..አቅም ማጣት፤
Low muscle tone     የጡንቻ መላላት (አለመጠንከር)
አር ኤች ኔጌቲቭ ከሆነች እናት የመጀመሪያ ልጅ ሆኖ የሚወለደው ህጻን የሚገጥመው ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሲሆኑ ህጻኑ የህክምና እርዳታ ከተደረገለት በሁዋላ የሚጠፋ ወይንም ወደ ጤናማ ሁኔታ የሚመለስ ነው፡፡
አንዲት እርጉዝ ሴት አንዲት የደም አይነትዋ Rh-negative ከሆነና በተመሳሳይ የባለቤትዋም የደም አይነት Rh-negative ከሆነ ምንም የሚያስከትለው ችግር ስለማይኖር መጨነቅ አይገ ባትም፡፡
ነገር ግን የባለቤትዋ የደም አይነት Rh-positive ሆኖ የእስዋ የደም አይነት ግን Rh-negative ከሆነ የአር ኤች አለመጣጣም ይከሰታል ማለት ሐክምዋ የተረገዘው ልጅ በማህጸን ውስጥ እያለ  የህጻኑን ደም ምር መራ እስከማድረግ ድረስ ክትትል በማድረግ በቀ ጣይ መደረግ የሚገባውን ያማክራል፡፡
አር ኤች አለመጣጣም በሚወለደው ልጅ ላይ የሚያስከትላቸው የተለያዩ ችግሮች መኖራቸውን ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
የሚወለደውን ልጅ አእምሮ ሊያበላሽ ይችላል፡፡
በህጻኑ ሰውነት ውስጥ ፈሳሽ ሊከሰት ይችላል፡፡
በአእምሮው የሚሰራቸው እንደ መንቀሳቀስ፤መስማት እና መናገር አለመቻል ያሉ ችግሮች፤
የተለያዩ የጤና ችግሮች
የደም ማነስ፤
ከላይ ከተመለከቱት በተጨማሪም በህጻኑ ላይ የሞት አደጋ ሊያስከትልም ይችላል፡፡ ጥሩ የህክምና ክትትል በሚደረግባቸው ሀገራት ይህ ችግር አልፎ አልፎ የሚከሰት ሲሆን አገል ግሎቱ በስኬታማነት በማይሰጥባቸው ሀገራት ግን ሰፋ ብሎ ይታያል፡፡


Read 13493 times