Tuesday, 14 December 2021 00:00

ከፀሐይና ከጨረቃ እምነትንና እውነትን ፍለጋ

Written by  (እንደ ሚትና ንድፈ ሃሳብ) ከአንለይ ጥላሁን ምትኩ
Rate this item
(2 votes)

 የሰው ልጅ በእምነትና በእውነት ላይ በመንገስ (በመቆም) ህልውናውን የሚገነባና የሚተክል የማንነቱ ባለዳ ነው፡፡ አንድም ሰሪ፣አንድም ተሰሪ ነው፡፡ የእምነቱም፤ የእውነቱም ማረጋገጫ ወይም መግለጫ ሀሰሳው ሩቅና ጠናና ነው፡፡ ከሙከራዎቹ መካከል ጨረቃንና ፀሐይን አንድም ከሚሰጡት ጥቅም፣ አንድም ከውበትና ሃይል (ብርሃን)፣ በርሱ (በሰው) ህይወት ላይ ያላቸው ከፍተኛ ተፅዕኖ ከልዕለ ሀይል  አንፃር (ይተረጉማል) ተተርጉሟል፡፡
በእኔ እምነት በቀደመው ዘመን ሚት ብቸኛው የእምነትና የእውነት ገላጭ የነበረ ይመስለኛል፡፡ በያዝነው የሰለጠነ ዘመን ደግሞ ሳይንስ የተጋድሎ ሜዳ በመሆን እውነትንም፤ እምነትንም ማስተንተኛው (መቅረጫ) ነው፤ለሰው፡፡ ስለሆነም ሰው ሙዳይ፣ሚትና ሳይንስ ደግሞ አለላ ናቸው። ታዲያ በቀላሉ የማይዘለቅበትን እልፍኝ በወፍ በረር (ከዚህም፤ ከዛም) ሰበዞቹን ለመቃኘት እሞክራለሁ፡፡ ከጨለማ ገፋፊዋ፣ የተመስጦና የውበት ተምሳሌት ጨረቃ እንጀምር፡፡
ሉናር ቴዮሪ {Lunar Theory}  የጨረቃን እንቅስቃሴ ከክዋክብት አንፃር በሂሳባዊ ስሌት የመግለፅ (የማስቀመጥ) እሳቤ ነው፡፡ ይህ ቴዮሪ የሚመሰረተው አንድም በቀደመ የእውቀቱ ግስጋሴ
(ማለትም ሂሳባዊ ስሌቶች፣ መሰረታዊ እሳቤዎች) እና መጠናዊ (quantitative) ስሌት፣ አሊጎሪዝምና የጂኦሜትሪ ስዕላዊ መግለጫ (የጨረቃን አቀማመጥ ከጊዜ ስሌት ጋር የሚያሳይ) ናቸው፡፡
ሉናር ቴዮሪ ከ2000 አመታት በላይ የዳበረ ታሪክ ያለው የምርምር ዘርፍ ነው። በመሆኑም ዘመናዊ ቅርፅ የያዘው ካለፉት ሶስት ክፍለ ዘመናት ወዲህ  ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ለመሰረታዊ ምርምርና ለቴክኖሎጂ ግብዓት (ዓላማ) አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ሉናር ቴዮሪ ከጥንት እስካለንበት 21ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ባደረገው የእድገት ግስጋሴ ውስጥ የማይተካ ሙያዊ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ምሁራን ከነስልጣኔ ዘመናቸው እንደሚከተለው ‹‹በእንግሊዘኛ›› ቋንቋ ሰፍረዋል፡፡
1.Greek/Hellenistic  {Hipparchus, Ptolemy} 2.Babylonian/Chaldean {Naburimannu,  Kidinnu, Soudines} 3.Arab {Ibn al-Shatir} 4.European, 16th to early 20th centuries {Tycho Brahe, Johannes Kepler, Isaac Newton, Edmond Halley, Johann Karl Burckhardt, Peter Andreas Hansen, Charles-Eugène Delaunay, John Couch Adams etc.} etc.
(Other notable mathematicians and mathematical astronomers also made significant contributions)
የተፈጥሮን ጉልበትም ሆነ ውበት በቋንቋና በስሌት ለመተርጎም የሚሄድበትን ርቀት ትዕምርታዊ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። እውነቱንና እምነቱን ፈለገ ወይም አሰሰ የምለው ለዚህ ነው፡፡ ሰው የእውነቱ ባሪያ ነውና፤ ይፈልጋል፡፡ ይጨብጣል፡፡ ያፀናል። አንድም በልማድ ሰነድነት፤ አንድም በንድፈሃሳብ ደረጃ ያሰርጻል፡፡ ይተክላል፡፡ ታዲያ የሚተክለው የራሱን እውነት ነው፤ የሚተረጎም እስከሆነ ድረስ፡፡
ሉናር ሚት (Lunar Myth)  የጨረቃ አምልኮት ወይም አምላክን የሚገልፁ ተረኮች ስያሜ ነው፡፡ በጥንታዊ ተረኮች አማካኝነት የጨረቃን እንቅስቃሴ፣ መጠን (ምዕራፎች) እና አቅጣጫ ሂደቶች የሚያስቃኝ አምልኮታዊ ስርዓትም ነው፡፡
የጨረቃ አምላክ (Lunar Deity) የጨረቃ አምላክ ወይም አማልክት የሚገለፅበት አምልኮ ሲሆን አንዳንዴ ደግሞ ልክ ህይወት እንዳለው ሰው ሊቆጠር ይችላል፡፡ ይህ አምልኮ እንደየባህሉ ልዩነቶች የተለያዩ አገልግሎቶችና ልማዶች (ስርዓቶች) አሉት፡፡ ነገር ግን በአመዛኙ ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ናቸው፡፡ በጥንታዊ እምነቶች ውስጥ በርካታ የጨረቃ አማልክቶች የመገኘታቸው ምስጢርም ይኸው ልዩነት ነው፡፡
አማልክቶቹ በተለያዩ ዓለማት በአይነትም ሆነ በፆታ የተለያዩ ናቸው፡፡ ለአብነትም የግሪኳ ሴት አማልክት ‹‹ሰሊን›› (selene) እና የሮማዋ አማልክት ‹‹ሉና›› (luna) እንዲሁም  የቻይናዋ ‹‹ቻንጊ›› (chang’e) ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በተጨማሪም አፍሪካዊ ከሆኑ የጨረቃ አማልክት መካከል አቡክ "Abuk" ተጠቃሽ ሲሆን የእምነት (የሚት) ስሙ ደግሞ ‹‹ዲንካ›› (Dink) ይባላል። የአማልክቱ ‹‹መለኮታዊ›› ተግባርም ውልደት (fertility)፣ ምግባር (morality)፣ ፈጠራ(creativity) እና ፍቅር (love) ናቸው፡፡ የእምነቱ በረከቶች በመሆናቸው  ለመመለኩ ምክንያቶች ናቸው፡፡
የጨረቃ  ምዕራፎች እና ግርዶሽ  መሬት ላይ ሆነን ጨረቃን ካየናት በአንፀባራቂ ‹‹ግራጫ›› ገፅታዋ ላይ የፀሐይ ብርሃን ተንፀባርቋል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ጨረቃ ብርሃን አታመነጭም፤ ከፀሐይ ያረፈባትን ታንፀባርቃለች እንጂ፤ ልክ መሬት ላይ በቀን እንደሚሆነው፡፡
በወር ውስጥ የምንመለከተው የተለያዩ የጨረቃ ገፅታዎች ‹‹የጨረቃ ምዕራፎች›› (lunar phases) ይባላል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ የጨረቃ ምህዋር (orbits) በመሬት ዙሪያ እና የመሬት ምህዋር (ንፍቀ ክበብ) ተፅዕኖ በፀሐይ ዙሪያ ስለሆነ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የእንቅስቃሴ ውጤት ነው፡፡
በጨረቃ ግርዶሽ ወቅት መሬት በፀሐይና በጨረቃ መካከል ትሆናለች፡፡ ይህም የፀሐይን ብርሃን በመገደብ (በማስቀረት) ጨረቃ በጥቅጥቅ ጨለማ እንድትዋጥ ያደርጋታል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ የመሬት ጥላ ጨረቃን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሊጋርዳት ይችላል፡፡ ይህም ሂደት በሁለት ይከፈላል፡፡ እነሱም ፡- ሙሉ ግርዶሽ እና ከፊል ግርዶሽ ናቸው፡፡ እያንዳንዳቸውን እንደሚከተለው እንመልከት፡፡
ሀ. ሙሉ ግርዶሽ (Total lunar eclipse)፡- ጨረቃ እና ፀሐይ ከመሬት በተቃራኒ አቅጣጫ ሲሆኑ የሚፈጠር የግርዶሽ አይነት ነው፡፡ ማለትም መሬት የፀሐይን ብርሃን ሙሉ በሙሉ በመጋረድ ጨረቃ ላይ ጥላዋን ታጠላለች፡፡
ለ.ከፊል ግርዶሽ (partial lunar eclipse)፡- የመሬት ከፊል ገፅታ ብቻ ጥላውን በጨረቃ ላይ ሲያሳርፍ የሚፈጠር የግርዶሽ አይነት ነው፡፡          
ሉናር የጊዜ አቆጣጠር ተምሳሌት
ሉናር የጊዜ አቆጣጠር ተምሳሌት ከሆኑት መካከል  የቻይና ሉናር የዘመን አቆጣጠር (Chinese Lunar Calendar) አንዱ ነው፡፡ ከሌሎች የሚለየው የፀሐይን ስርዓት ደርቦ መጠቀሙ ነው፡፡ የወር ለውጡ የሚመሰረተው አንዴ በፀሐይ ሌላ ጊዜ ደግሞ በጨረቃ ስርዓቶች ላይ ነው። የወሩ ርዝማኔ የሚመሰረተው በሁለቱ አዲስ ጨረቃዎች መካከል ባለው የጊዜ ርቀት አማካኝነት ነው፡፡ ይህ የጨረቃ ወር ስያሜ የተወሰደው ከፀሐይ ስርዓት (solar system) ነው፡፡
የፀሐይ ሚት (Solar Myth) የፀሐይ እምነት ወይም አምላክ ተረክ (ሚት) ነው፡፡ ይህም በባህላዊ ተረኮች መነሻነት የፀሐይን እንቅስቃሴ (motion)፣ ተፅዕኖ እና አቅጣጫ መግለጫ ሙያም ነው፡፡ ይህን እሳቤ የሚያጠና የሳይንስ ዘርፍ ሶላሪዝም (solarism) ይባላል፡፡ ሶላሪዝም የጥንት ፎክሎራዊ ተረኮችን እና ሌጀንዶችን መነሻ በማድረግ የተፈጥሮንና በዋናነት የፀሐይን እንቅስቃሴ፣ መጠን የሚመረምር፣የሚፈክርና የሚተነትን የጥናት መስክ ነው፡፡
እንደ ‹‹ሙለር›› (Müller’s) ገለፃ ከሆነ፤ ሶላር ሚት የተገኘው ወይም የተወለደው ከኢንዶ-ኤሮፓ የቋንቋ ጥናት ነው፡፡ በሙለር እምነት ‹‹ሳንስክሪት›› ቋንቋ በርካታ የፀሐይ አማላክትን ስሞች ወይም ስያሜዎች የሚጠቀም ሲሆን ይህም ሁኔታ በሌሎች ቋንቋዎች በተመሳሳይ መልኩ አገልግሎት ላይ መዋሉን ታዝቧል፡፡ ይህም የሚትን ድንበር ዘለል (ተሻጋሪነት) ባህሪ ጠቋሚ መሆኑን ታዝቧል፡፡
የፀሐይ አምላክ (Solar Deities)  በፀሐይ የተወከለ አምላክ ወይም አማልክት ሲሆን የሐይል እና የጥንካሬ ተምሳሌት ነው። የፀሐይ እምነት ወይም አምልኮ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በተለያየ መንገድ ወይም ስልት የተገለጠ እውነታ ነው። ለአብነትም በአፍሪካ እንደ ‹‹ማጀክ›› (magec) (Tenerife goddess of the sun and Light) እና ‹‹ኢንያንጋ›› ደግሞ በበርካታ ህዝብ ዘንድ የጨረቃ አምላክ ተደርገው ይመለካሉ፡፡ እንዲሁም በግብፅ ሚቶሎጂ ውስጥ ‹‹ኼፕሪ››(kheori) ደግሞ የፀሐይ መውጫ፣ የፈጠራ እና የአዲስ ሕይወት ተምሳሌት (አምላክ) ሆኖ ይመለካል። እንዲሁም ‹‹ራ›› (Ra) የፀሐይ አምላክ ነው። ከፀሐይ አማልክቶች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
African {Anyanwu, Igbo god believed to dwell in the Sun, Magec, Tenerife goddess of the Sun, iNyanga, Zulu people, goddess of the Moon}
Egyptian mythology {Ra, god of the Sun,Sekhmet, goddess of war and of the Sun, sometimes also plagues and creator of the desert,Sopdu, god of war and the scorching heat of the sun}
Aztec mythology [edit] {Huitzilopochtli, god of the Sun and war,Nanahuatzin, god of the Sun}
በአጠቃላይ ሉናር እና ሶላር ሚት ቴዮሪ ለበርካታ የሙያ ዘርፎች ግብዓት የሚሆኑ እሳቤዎች፣ ምልከታዎች  ያቀፈ ነው፡፡ በድህረ ዘመናዊነት የሳይንስ ምርምር አማካኝነት የሙያዎችን ድንበር የጣሰና በከፍተኛ ደረጃ ያስተሳሰረ እሳቤ ነው፤ ሚት፡፡ የተለያዩ ተረኮች ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ግለሰባዊ ፋይዳ እንደ ሳይኮሎጂ፣ አንትሮፖሎጂ፣ ሶሾሎጂና ፍልስፍና እንዲሁም ነገረ መለኮት ወዘተ…ያሉ ሙያዎች ጉዳይ (ተጠኝ) የሆነ ሙያ ነው፡፡
ሚት በባህሪው ምናባዊ ተረክ በመሆኑ ኩሸት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተምሳሌታዊ በመሆኑ ከዘወትራዊ ኑሮ የራቀና የጠነነ ነው፡፡ በመሆኑም ተረኮቹ እውነት ሆነው መተረካቸው የእምነት መጣረስ ያስከትላሉ የሚል እይታ አለኝ፡፡ የሀይማኖቶቹ አጀማመርም ሆነ ቀኖና መሰረት ማጠየቂያም ጭምር ነው፡፡
ከአዘጋጁ፡- ጸሃፊውን በኢሜይል አድራሻው፡- This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ማግኘት ይቻላል።

Read 8397 times