Saturday, 11 December 2021 13:01

“ከፈተና የተገኘ ትምህርት ከፅናት የተወለደ ተስፋ “የጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(2 votes)

   በምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን በየወሩ የሚካሄደው የኪነ ጥበብ ምሽት የዚህ ወር መሰናዶ “ከፈተና የተገኘ ትምህርት ከፅናት የተወለደ ተስፋ” በሚል ርዕስ ሰኞ ታህሳስ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ ጊዮን ሆቴል ውስጥ በሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ዎክ ይካሄዳል። በዕለቱም ወግ፣ዲስኩር፣ግጥምና ሙዚቃ የሚቀርብ ሲሆን፣አቶ ጣሂር ኢብራሂም፣ ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣በድሉ ዋቅጅራ(ዶ/ር)፣ ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ፣ አበባው አያሌው (ረ/ፕ)፣መምህርት ዕፀገነት ከበደ፣ አርቲስት ተስፋዬ ማሞ፣ ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ፣አርቲስት ተፈሪ አለሙና ገጣሚ ምንተስኖት ግዛው ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል፡፡
ዲፕሎማት ባንድ መርሃ ግብሩን በሙዚቃ የሚያጅብ ሲሆን፣ የመግቢያ ዋጋው 100 ብር እንደሆነና የመግቢያ ትኬቶቹም በጃዕፋር፣ አይናለም፣ዮናስ መፅሀፍት መደብሮች፣ በጣይቱ ሆቴልና ከዛንቺስ በሚገኘው ጆሲ ልብስ ስፌት ቤት እንደሚገኙ አዘጋጁ ጋዜጠኛ ምስክር ጌታነው ገልጿል፡፡

Read 21569 times