Saturday, 04 December 2021 13:08

የአሜሪካና ብሪታኒያ ኤምባሲዎች ህዝብን ከማሸበር እንዲቆጠቡ ተጠየቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

 የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት የአሜሪካና የብሪታንያ አምባሳደሮች ከሚያሰራጫቸው “ሽብር ፈጣሪ” የማስጠንቀቂያ መልዕክቶች ማብራሪያ እንዲሰጡት ጠየቀ።
በጋራ ም/ቤቱ በታላቋ ብሪታኒያ የቡና ንግድ ኪንግደምና ሰሜን አየርላድ አምባሳደር ሚስተር  አላስታየር ማክፋይልና ለተባበረው አሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፖሊ በፃፈው ደብዳቤ ኢምባሲዎቹ በኢትዮጵያ ባለው ጦርነት ጉዳይ በተደጋጋሚ ተጨባጭ ያልሆኑ በዜጎች ላይ ሽብር የሚፈጥሩ መረጃዎችን እያሰራጩ መሆኑን አመልክቷል።ይህ የሽብር መረጃም አሜሪካም ሆነች ብሪታንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን  የረጅም ዘመናት የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ያላገናዘበና የሃገሪቱን ስትራቴኪካዊ አጋርነት ከግምት ያስገባ መሆኑን የጋራ ም/ቤቱ በደብዳቤው አመልክቷል።
የጋራ ም/ቤቱ ለአሜሪካ አምባሳደር በጻፈው ደብዳቤው በበርካታ የታሪክ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያ በክፉ ጊዜ የአሜሪካንን እገዛ ሚያስፈጋት ጊዜ እርዳታዋን እንደማታገኝ በተቃራኒው ኢትዮጵያን ለማዳከም ከሚሰሩት ሃይሎች ጋር ስትተባበር እንደምትገን በደብዳው ተመልክቷል።“በአሁኑ ወቅትም የአሜሪካ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በአጋርነት መቆም ሲገባው የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጭምር በመጣል፤ ሽብርተኛ ቡድንን ከህጋዊ መንግስት ጋር እኩል በንጽጽር በመመልከት፣ በሠብአዊነት ሰበብ በኢትዮጵያውያን መሃል ልዩነት በመፍጠርና እርስ በእርስ በመከፋፈል እንዲኖር በማድረግ የተጠናል የሃሰት ፕሮፖጋንዳ በመንዛት፣ የሃገራችንን ስም በተደጋጋሚ በክፉ በማንሳት በዓለም ፊት ተደማጭነቷ እንዲደበዝዝ በመስራት መንግስትም ከህወሃት ያልተናነሰ በደል እያደረሰ ይገኛል ብሏል የጋራ ም/ቤቱ በደብዳቤው። የጋራ ምቤቱ ለብሪታንያ አምባሳደር በጻፈው መልዕክቱም በተመሳሳይ የብሪታንያ መንግስት ለህውሃት መወገኑን አመላክቶ ኮንኗል።
ኢምባሲዎቹ በየጊዜው በሚያወጧቸው ሽብር የሚነዙ መግለጫዎች የሃገሪቱን ወዳጅነት በእጅጉ ሊሸረሽሩ የሚችሉ ተግባራት ውስጥ መዘፈቃቸውን ያመለከተው ደብዳቤው በቀጣይ  የአሜሪካም ሆነ የብሪታኒያ ኤምባሲም ሆነ የየሀገራቱ መንግሰት በከተማ ውስጥ ሽብር ከመንዛት እንዲቆጠቡ፤ የአፍሪካውያንን ጉዳይ አፍሪካውያን እንድንፈታው የራሳችንን ጉዳይ ለራሳችን እንድትተውልን እንጠይቃለን ብሏል የጋራ ም/ቤቱ። በደብዳቤው ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡን ያነጋገርናቸው የጋር ም/ቤቱ ም/ሰብሳቢ አቶ ጌትነት አምባሳደሮቹ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ መጠየቁንና ምላሻቸው እየተጠበቀ መሆኑን ለአዲስ አድማስ አስታውቀዋል።


Read 11583 times