Saturday, 27 November 2021 14:41

የአቤል ተስፋዬ ዜማ በቢልቦርድ ታሪክ የምንጊዜም መሪ ሆኗል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

    የወቅቱ የአለማችን የሙዚቃ ኮከብ እንደሆነ የሚነገርለት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ፣ ከሁለት አመታት በፊት ለአድማጮቹ ያቀረበው ብላይንዲንግ ላይትስ የተሰኘ ተወዳጅ ነጠላ ዜማ፣ በቢልቦርድ የሙዚቃ ሰንጠረዥ ቁጥር አንድ ሆኖ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ የምንጊዜም ምርጥ ዜማ ለመሆን መብቃቱ ተዘግቧል፡፡
በቅጽል ስሙ ዘ ዊክንድ በመባል የሚታወቀው ኢትዮ-ካናዳዊው የ31 አመት ድምጻዊ አቤል ተስፋዬ፣ እ.ኤ.አ በ2019 ህዳር ወር ላይ የለቀቀው ብላይንዲንግ ላይትስ የተሰኘ ይህ ተወዳጅ ነጠላ ዜማ፤ በቢልቦርድ ምርጥ 100 ሙዚቃዎች ዝርዝር ላለፉት 90 ተከታታይ ሳምንታት የአንደኛነት ስፍራን ይዞ መዝለቁ ለዚህ ክብር እንዳበቃው ነው ቶሮንቶ ኒውስ የዘገበው፡፡
በቢልቦርድ የ63 አመታት ታሪክ የምንጊዜም መሪ ሙዚቃ ሆኖ ተመዝግቦ የነበረው በ1960ዎቹ ለአድማጭ የበቃው ዘ ትዊስት የተሰኘ የቻቢ ቼከርስ ተወዳጅ ዜማ እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው፤ ይህ ዜማ በ2008 ያገኘውን ይህን ክብሩን ሰሞኑን ለብላይንዲንግ ላይትስ አስረክቦ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ ማለቱን አመልክቷል፡፡

Read 1773 times