Saturday, 27 November 2021 14:33

ዳሽን ባንክ ለአምስት ዋና ዋና ቦታዎች ሀላፊዎችን ሾመ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

    ዳሽን ባንክ ለአምስት ቁልፍ ቦታዎች ሀላፊዎቹን መሾሙን አስታወቀ፡፡ ባንኩ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የአምስቱን ሀላፊዎች ሹመት ለብሔራዊ ባንክ አቅርቦ ብሔራዊ ባንክ አምስቱን ምክትል ስራ አስፈጻሚዎች ሹመት ማጽደቁን ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ባንኩ ሰሞኑን የስትራቴጂ እቅዱን መከለሱንና የባንኩን መዋቅር መልሶ ማዋቀሩን የገለፀው የባንኩ መግለጫ ከነዚህ ስራዎቹ በኋላ ለአምስቱ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች በሙያቸውና በስራ ልምዳቸው የተመሰገኑ ሀላፊዎቹን መሾሙን አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት አቶ አየለ ተሾመን የቢዝነስ ባንኪንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ኢየሩሳሌም ዋጋውን የሰው ሀብት ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ፣መስፍን በዙን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ ሙሉጌታ አለባቸውን፣የስትራቴጂና የኢኖቬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ዮሃንስ ሚሊዮንን ደግሞ የዲጂታል ባንኪንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አድርጎ መሾሙን ነው ባንኩ ያስታወቀው፡፡
 እንደባንኩ ገለጻ ከተሿሚዎቹ አራቱ ከ18-30 ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸውና ከአቶ አየለ በስተቀር ሶስቱ በዳሽን ባንክ ከስር ጀምረው ባንኩን በቅንነትና በታማኝነት በማገልገል እያደጉ መጥተው ለዚህ የደረሱ ሲሆን አቶ አየለ ተሾመ ግን በባንክ ሙያ ዘርፍ ከ30 ዓመት በላይ ልምድ ያካበቱ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የዲጂታል ባንኪንግ ዘርፍ ምክትል ዋና  ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት ዮሃንስ ሚሊዮን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዲጂታል ባንኪንግ ዘርፍ ከጀማሪነት ጀምሮ አሁን ወደ ዳሽን ባንክ እስከ ተቀላቀሉበት ጊዜ ድረስ ያገለገሉ መሆናቸውንና አሁንም በዳሽን ባንክ በተሸሙበት ሀላፊነት ባንኩንና አገራቸውን በታማኝነት ያገለገሉት ተብሎ መታመኑን ባንኩ መግለጫው አስታውቋል፡፡

Read 1889 times