Saturday, 27 November 2021 13:49

ረቡእ-December 1 የአለም ኤችአይቪ ኤይድስ ቀን

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

   መጪው እሮብ እ.ኤ.አ ዲሴምር 1/2021 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ህዳር 22/2014 የአለም የኤችአይቪ ቀን ነው፡፡ ይህ ቀን በመላው አለም ስለኤችአይቪ ኤድስ ሰዎች እንዲነጋ ገሩ፤እንዲመካከሩ፤እንዲወስኑ ባጠቃ ላይም ስለኤችአይቪ ቫይረስ ከፍ ያለ ንቃተ ህሊና እንዲፈጥሩ ፤ስርጭቱን ለመግታት የተቻለውን ሁሉ እንዲያደ ርጉ፤ አድሎና መገለል እንዲያስወ ግዱ እና ስለወደፊቱ ህይወት አቅጣጫ እንዲተልሙ፤የተሸለ አቅጣጫን ለወደ ፊት እንዲያልሙ…ወዘተ ሲባል አለም አቀፍ ቀን እንዲሆን የተሰየመው እ.ኤ.አ ከ1988 ጀምሮ ነው፡፡
የአለም ኤችአይቪ ቀን እ.ኤ.አ ዲሴምበር 1 እንዲሆን በአለም የጤና ድርጅት ሲወሰን በአለም ላይ ሀገራት በብሔራዊ ደረጃም ይሁን በአለም አቀፍ ደረጃ ስለኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭትና ስርጭቱንም ስለመግታት እንዲሁም ሰዎች በህክምና ምርመራ እራሳቸውን እንዲያውቁ እና ተያያዥ ስለሆኑት ጉዳዮች የሀሳብ እና ልምድ ልውውጥ እንዲደረግ ለማስቻል ጭምር ነው፡፡  
አለም አቀፉ የኤችአይቪ ቀን እ.ኤ.አ በአለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከበር ከ90,000-150,000 የሚሆኑ ሰዎች በኤችአይቪ ቫይረስ የተያዙ የነበሩ ሲሆን ከዚያ በሁዋላ በሁለት አስርት አመታት ውስጥ ከሰላሳ ሶስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ይገኝ እንደነበር ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ ኤችአይቪ ኤይድስን በሚመለከት ሪፖርት ከተደረገበት እ.ኤ.አ 1981 ጀምሮ ወደ ሀያ አምስት ሚሊዮን ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተረጋግጦአል፡፡
ከላይ የተገለጹትን መረጃዎች ምክንያት በማድረግ እና ለህመሙ መድሀኒት ከማግኘት ጥረት ጋር በተያያዘ ስለህመሙ ንቃተ ህሊናን የማስፋት እንዲሁም የባህርይ ለውጥን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ስራ መሰራት እንዳለበት እና ህብረተሰብን ማስተማር ፤የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ጭምር ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
የአለም ኤችአይቪ ኤይድስ ቀን እ.ኤ.አ በ2021 ዲሴምበር 1/2021 ወይም ህዳር 22/2014/ የፊታችን ረቡእ እለት ይውላ ል፡፡የአለም ኤችአይቪ ቀን በየአመቱ እንዲታሰብ ወይንም እንዲከከበር ከተወሰነ ጊዜ ጀምሮ በየአመቱ የተለያዩ ግቦችን ለማሳካት እንዲያመች ሲባል የሚሰጡ ስያሜዎች ነበሩ፡፡

የዓለም ኤድስ ቀን 2021 መሪ ሃሳብ በእንግሊዝኛው End inequalities. End AIDS የሚል ነው፡፡ ወደ አማርኛ ሲመለስ “አለመመጣጠንን አስወግድ። ኤድስ ያብቃ “ የሚል ይሆናል፡፡ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ያልተደረሰባቸውን ሰዎች ለመድረስ ልዩ ትኩረት በመስጠት የዓለም ጤና ድርጅት እና አጋሮቹ አስፈላጊ የሆኑትን የኤችአይቪ አገልግሎቶች ተደራሽነት ፤እኩልነት ማጉላት እንዲቻል የዘንድሮው መሪ ቃል ያሳስባል፡፡
እ.ኤ.አ 2021/የአለም ኤችአይቪ ቀን ሲውል እስከ 2020/ድረስ ያለውን እውነታ ወደሁዋላ ተመልሶ የአለም የጤና ድርጅት እንደሚከተለው ገልጾታል፡፡
በአለም ላይ እስከ 2020 ድረስ የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች መጠን------37,700,000
በኤችአይቪ ቫይረስ ምክንያት እስከ 2020 ድረስ የሞቱ----680,000
በ2020 በአዲስ በቫይረሱ የተያዙ -----1,500,000--ሰዎች
73 % ታዳጊዎች ቫይሱ በደማቸው ስላለ በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ፀረ ኤችአይቪ (ART) የሚወስዱ መሆኑ በ2020 ተመዝግቦአል፡፡
      World AIDS Day 2021፡- End inequalities. End AIDS
የአለም ኤችአይቪ ቀን እ.ኤ.አ ዲሴምበር 1/2021/ ኤችአይቪን በሚመለከት ያለውን የአገልግሎት አለመመጣጠን ማስወገድ፤ኤችአይቪን እንዲያበቃ ማድረግ የሚል መሪ ቃል አለው፡፡
ኤችአይቪ ዛሬም በአለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ የጤና ችግር ተደርጎ የሚወሰድ ቫይረስ ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ ቫይረሱን ለመከላከል ብሎም ለማስወገድ ብዙ ተግባራት ቢከናወኑም በ2020 በቫይረሱ ዙሪያ የተያዙት እቅዶች እውን እንዳይሆኑና ዛሬም ቫይረሱ ሰዎችን እየጎዳ እንዲቀጥል ምክንያት ሆኖአል፡፡
ሰዎችን ተደራሽ አለማድረግ፤በእኩልነት አለማየት የመሳ ሰሉ ነገሮች ኤችአይቪ የአለም ጤና ስጋት እንደሆነ እንዲቀጥል አስችሎታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኮሮና ቫይረስ ሰዎችን በጤ ናው አገልግሎት በእኩ ልነት ተመጣጣኝ በሆነ መንገድ መርዳት የሚ ለውን አሰራር በአ ለም አቀፍ ደረጃ አሳይቶአል፡፡ ኮሮና ቫይረስ በቀናት ደረጃ ሰዎችን አፋጥኖ የሚገድል በመ ሆኑ የጤና አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በቫይረሱ ለተያዙ ሰዎች ተመጣጣኝ በሆነ መንገድ አገልግሎቱ እንዲሰጥ ያስ ገደደበት ሁኔታ ሲኖር የኤችአይቪ ቫይረስ አገልግሎት ግን ከዚያ በተለየ ስለነበር ለብዙዎች ህልፈት አስተዋጽኦ ማድረጉ እሙን ነው፡፡ ቫይረሱ በደም ውስጥ መኖሩም ምን ያህል አስቸ ጋሪ እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡  
World AIDS Day 2021 is “End inequalities. End AIDS”. 
የአለም ኤችአይቪ ቀን ዲሴምበር 1/2021
 ኤችአይቪን በሚመለከት ለሚሰጠው አገልግሎት አለመመጣጠን  ያብቃ፡፡
     የኤችአይቪ ስርጭት ያብቃ፡፡
ከላይ ያነበባችሁት መልእክት ዲሴምበር 1 የፊታችን ረቡእ ለሚውለው ለ2021 የአለም ኤችአይቪ ቀን የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆን የተወሰነ መሪ ቃል ነው፡፡
የአለም የጤና ድርጅት እና ተባባሪ አካላት ለወደፊት ኤችአይቪን ለመግታት የሚሰጡ አገልግሎቶች ለሁሉም ሰው በእኩልነት እንዲሆን እና ትኩረት ያላገኙ እና ወደሁዋላ የቀሩትን ሰዎች በማፈላለግ ወደ አገልግሎቱ በማምጣት አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ እንደሚገባ በመረጃው ጠቁሞአል፡፡
በዲሴምበር 1/ 2021 የአለም የጤና ድርጅት ለአለም መሪዎችና ህዝቦች ጥሪ አድርጎአል፡፡ ጥሪውም ኤችአይቪ ኤይድስን ለማስቆም በጋራ እንሰለፍ፤ በጋራ እንቁም የሚል እና ችግሩን ለመቋቋም እንዲቻል ህዝ ቦችም የባህርይ ለውጡን እውነተኛ ከማድረግ ባሻገር ተቋቁሞ ለውጥ ለማምጣት እንዲቻል ነው፡፡ በዚህ መልእክትም ወሳኝ የሆነ መልእክት እንደሚከተለው ተቀምጦአል፡፡
ኤችአይቪ ኤይድስን ለመከላከል እንደገና መወሰን ያስፈልጋል፡፡ የኮቪድ 19ን ወረርሽኝ ለመከላከል በአለም ዙሪያ በእኩልነት እና በተመሳሳይ መንገድ የተሰሩ ስራዎችን ሞዴል በኤችአይቪ ላይ በመተግበር ሁሉም የአለም ክፍል ኤች አይቪ የጤና ችግር ከመሆን እንዲላቀቅ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
ኤችአይቪ እና ኮሮና ቫይረስን በጋራ መከላከል ይገባል፡፡ የኮሮና ቫይረስ የኤችአይቪ ቫይረስ ላለባቸው ሰዎች የከፋ የጤና ችግር እንዳያደርስ ሁሉም መከላከል ይገባዋል፡፡
አለመመጣጠንን ለማስወገድ ፤እኩልነትን ለማረጋገጥ ትኩረት መስጠት ሌላው ትኩረት የሚሻ ነው፡፡ ሁሉም፤የትም፤ያለ ሰው ኤችአይቪን ለመከላከል የሚያስችለውን ፤ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ የሚያደርገውን ምርመራ፤አገልግሎትና ክትትል የኮሮና ቫይረስን ክትባት እና አገልግሎት ጨምሮ በእኩልነት ለማግኘቱ እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡  
ወደሁዋላ የተገፉ ወይንም ያልተመጣጠነ አገልግሎት የሚያገኙ ሀገራትና ሰዎች ላይ ጠንክሮ መስራት ሌላው የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡ የአለም የጤና ድርጅት የሚያሳስበው ሀገራት እና ህዛቦች በአለም አቀፍ ደረጃ ኤችአይቪ ኤይድስን ለመከላከል የሚደረገውን አገልግሎት እንዲያገኙ አሰራሮችን ማስተካከል እንደሚ ገባ ነው፡፡ ይህም በየሀገራቱ ያሉ ለችግሩ የተጋለጡ ህጻናት ፤ሴቶች እና ወንዶችን ባጠቃላይም ሰው የሆነን ሁሉ የሚመለከት ነው፡፡


Read 12012 times