* የፖለቲካ መሪዎች ወጣቱን የአገር ችግር ለመፍታት እንጂ ችግር ለመፍጠር መጠቀም የለባቸውም።
-ሳድሃጋኪ-
* ሁልጊዜ መጪውን ዘመን ለወጣቱ መገንባት አንችልም፤ ነገር ግን ወጣቶቻችንን ለመጪው ዘመን መገንባት እንችላለን።
-ፍራንክሊን ዲ.ሩስቬልት-
* ለወጣቱ እውነት መናገርን አስተምረው፤ ሰላም ምን ሊፈይድ እንደሚችል አሳየው።
-ራኪም-
* የእያንዳንዱ አገር መሰረት የወጣቱ ትምህርት ነው።
-ዲዮጄነስ-
* ከ ሞላ ጎ ደል ሁ ሉም ታ ላላቅ ነ ገሮች የተከናወኑት በወጣቶች ነው።
-ቤንጃሚን ዲዝራኤሊ-
* ወጣትነት የተፈጥሮ ስጦታ ነው፤ እርጅና ግን የጥበብ ሥራ ነው።
-ስታኒስላው ጄርዚ ሎክ-
* ሽማግሌዎች ጦርነትን ያውጃሉ። የሚዋጋውና የሚሞተው ግን ወጣቱ ነው።
- ኸርበርት ሁቨር-
* ወጣትነት የሚመጣው በህይወት ዘመን
አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
-ሔነሪ ደብሊው. ሎንግፌሎው-
* ወጣቶች የሚፈልጉት ተቺዎችን ሳይሆን
አርአያዎችን ነው።
-ጆን ውድን-
* የዛሬዎቹ ወጣቶች የነገ መሪዎች ናቸው።
-ኔልሰን ማንዴላ-
* ለወጣትነት ዕድሜ ህልሞችህ ታማኝ ሁን።
-ፍሬድሪክ ሺለር-
* ወጣቱ የመጪው ዘመን ተስፋችን ነው።
-ጆሴ ሪዛል
Published in
ጥበብ