Thursday, 25 November 2021 07:01

የግጥም ጥግ

Written by  ነፃነት አምሳሉ
Rate this item
(1 Vote)

  ጥቁር እንቁ!
            

ፍጥረት ለ..ሽ ብሎ ~ ሆኖ በድብታ
አልጋ ላይ ሲንፏቀቅ ~ ሆኖ በሸለብታ
ከሞቀው መኝታ - ብንን ብላ ነቅታ
መለከት የነፋች - ነፃነት ተጫምታ
ብርሃን የለኮሰች ~ ሌሊቱን ሳትፈራ
ማን ነበረች እቴ ~ ያቺ የሀገር አውራ ?!
ሮጣ ....... ሮጣ ........ ሮጣ
ልጆቿን አራውጣ
አቀበቱን ወጥታ
ቁልቁለቱን ወርዳ
ሙያ ጥበብ ሰጥታ ~ ሆሄ ፊደል ቀርጻ
በዜማዎች ማእበል - ስጋ ነፍስን ጠምቃ
ቀለም አስበጥብጣ ~ ስ እል አስተምራ
ህንጻ ያሰራችው ........................
ማን ነበረች እቴ ~ ያቺ እማወራ ?!
አጃኢብ ነው መቼም - ዛሬ ምናብ መስሎ
የእምዬ ውለታ
ተቆጠረ አሉኝ
እንደ እፉዬ ገላ - ለሰው መዳፍ ቀልሎ !
ውብ ዜማ ቀምራ ~ ነፍስ እየመከረች
ሰውን ከፈጣሪው ~ እያስተሳሰረች
በደም ቤዛ ጸድቃ - በአጥንት ቤትዋን ሰርታ
ለጥቁር ህዝብ ደምቃ - ኮከብ ሆና በርታ
እንግዳ አክብራ ~ አልጋ የለቀቀች
ከአብርሃም ተምራ
የሰው እግር አጥባ
በነፍስዋ መንና- ሰው ሳትሆን ሰው መስላ ~
ማነች የጸደቀች ?!
እንደ ነብር ገላ ገላዋ ተጊጦ
ዥንጉርጉር ውበትዋ ከቀለማት በልጦ
በቆዳ በቀለም ~ በቋንቋ ተዋድዳ
ዘመንን የዋጀች ...................
እስቲ ሀገር ፈልጉ ~ ገብታችሁ ከጓዳ !
አጥንት እየፈጨ ~ ዘሩን ያልቆጠረ
ተዋልዶ ተጋምዶ ~ ሺ ዘመን የኖረ
የአንዱ ደም ተቀድቶ ~ ቢታይ በዓይናችን
እኔ ውስጥ አንተ ነህ
አንቺ ውስጥ እኔ ነኝ ~ ውዴ በደማችን !
ዛሬ በተቃርኖ ~ ብትሆን ጅራት ጭራ
ቀን ዘመመ ብዬ
ተስፋ አልቆርጥም እኔ ~ በእምዬ ባንዲራ !
አዳፋ ቢሆንም ~ ነትቦ ተበጣጥሶ
ጽልመት ቢፎክርም ~ የሀዘን ልብሱን ለብሶ
ቀን ቢጎድልም ከቶ ~ ከጊዜ ተፋልሶ
ደሀ ስለሆነች .........................
ሀገሬን ጠላኋት ! ~ አይባልም ደርሶ !
በተራሮች አናት ~ ለሀገር የወደቁ
ድንበር አስከብረው ~ ወራሪን ያራቁ
የኚያን ጀግኖች አጽም ~ እያየሁ በሩቁ
አፈሳለሁ ዕንባ ....................
ነፃነት ለብሼ …………………..
ደምቄያለሁ እኔ - ጀግናው ጥቁር እንቁ

Read 1583 times