Saturday, 13 November 2021 13:14

“የታፈነ ሲቃ” የግጥም ስብስብ መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በ14 እና በ15 ዓመት  ዕድሜ ታዳጊዎቹ ዙፋን ምትኩና ሳምሶን ተክሌ የተሰናዳውና “የታፈነ ሲቃ” የተሰኘ መጠሪያ ያለው የግጥም ስብስብ መጽሀፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡የአዳማ ነዋሪ የሆኑት ታዳጊዎቹ በግጥሞቻቸው ስለ ሀገር፣ ስለ ፍቅር፣ ስለ አገር ተፈጥሮና ፀጋ ፣ስለ እናት፣ አጠቃላይ ስለ ህይወትና ስለ በርካታ ጎዳዮች ያላቸውን መረዳት በግጥሞቻቸው ለመግለፅ ሞክረዋል፡፡
ታዳጊዎቹ በእውቁ የፊልም ባለሞናያ  “ባማ” ኢንተርቴይመንት መስራች አርቲስት ገዛኸኝ ጌታቸው የፊልም ት/ቤት ተማሪዎች ሲሆኑ ፣አርቲስቱ ታዳጊዎቹ ከፊልም ባሻገር ለግጥም ያላቸው ተሰጥዖና ፍላጎት በመረዳት በገንዘብና በሀሳብ ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር ግጥማቸውን የህትመት ብርሀን እንዲያይ ማድረጉን በመግለፅ በመግቢያቸው ላይ አመስግነውታል ፡፡ከ40 በላይ ግጥሞችን ያካተተው መፅሀፉ በ60 ገፅ ተቀንብቦ በ90 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡     



Read 1708 times