Tuesday, 09 November 2021 00:00

በ2020 ብቻ በአለም ዙሪያ 62 ጋዜጠኞች ተገድለዋል ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው የፈረንጆች አመት 2020 ብቻ በመላው አለም 62 ጋዜጠኞች በሙያቸው ስላገለገሉ ብቻ መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
እ.ኤ.አ ከ2006 እስከ 2020 በነበሩት አመታት በመላው አለም ከ1 ሺህ 200 በላይ ጋዜጠኞች መገደላቸውን ያስታወሰው ተቋሙ፣ ግድያዎቹን ከፈጸሙት መካከል 90 በመቶ ያህሉ ለህግ እንዳልቀረቡና እንዳልተቀጡም አክሎ ገልጧል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ በበኩላቸው፤ በጋዜጠኞች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችንና ወንጀሎችን ለማስቀረት በየአመቱ የሚከበረውን አለማቀፍ የንቅናቄ ቀን በማስመልከት ባለፈው ማክሰኞ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ግጭቶችን በሚዘግቡበት ወቅት ህይወታቸውን የሚያጡ ጋዜጠኞች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም ከግጭት ውጭ የሚገደሉ ጋዜጠኞች ቁጥር ግን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡
ሴት ጋዜጠኞች በተለየ ሁኔታ ለአደጋ ተጋላጭ መሆናቸውን የጠቆሙት ዋና ጸሃፊው፤ በበርካታ አገራት ሙያዊ ስነምግባርን ባከበረ መልኩ በሙስና፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችና በመሳሰሉ ጉዳዮች ዙሪያ የምርመራ ዘገባዎችን መስራት የጋዜጠኞችን ህይወት የከፋ አደጋ ላይ የሚጥል አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑንም ገልጠዋል፡፡


Read 1025 times