Print this page
Saturday, 06 November 2021 00:00

የአሜሪካው መልዕክተኛ ከምክትል ጠ/ሚር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያዩ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ባለፈው ረቡዕ  አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፈር ፌልትልማን ከምክትል ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን፣ ከመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይና  ከገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ጋር ተወያዩ፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ ለተፈጠረው ጦርነት መፍትሔ ለማፈላለግ ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የተባሉት ፌልትማን ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በተጨማሪ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ጋርም በጉዳዩ ላይ መምከራቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ አስታውቀዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከባለስልጣናቱ ጋር በዝርዝር የተወያዩበት ጉዳይ አልተገለጸም፡፡
ፌልትማን አንደኛ ዓመቱን ያስቆጠረው የሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ  ሲሆን በሰሜኑ የአገራችን ክፍል እየተካሄደ ከሚገኘው ጦርነት ጋር በተያያዘ ሁሉም የተፋላሚው ወገኖች የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ልዩ መልዕክተኛው ከአፍሪካ ህብረትና ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር  ባካሄዱት ውይይት ጦርነት በሚቆምበት ጉዳይ ሳይመክሩ እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡
የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ ሁሉም ወገኖች ወደ ውይይት እንዲመጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Read 9551 times
Administrator

Latest from Administrator