Friday, 29 October 2021 00:00

ካራካስ የአለማችን ቁጥር 1 የቆነጃጅት ከተማ ተባለች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

  መኒ ዩኬ የተባለው ተቋም ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ጥናት፣ የቬንዙዌላዋ ካራካስ ከአለማችን ከተሞች መካከል ቆንጆዎችን በማፍለቅ አቻ የማይገኝላት ቀዳሚዋ ከተማ ተብላ በአንደኝነት መቀመጧን ዴይሊ ሜይል ድረገጽ ዘግቧል፡፡
ተቋሙ በተለያዩ አለማቀፍ የቁንጅና ውድድሮች አሸናፊዎች የሆኑ 500 ቆነጃጅትን የትውልድ ከተማ በማጥናት ባወጣው ሪፖርት መሰረት 10 ቆነጃጅቷን ያስሸለመችው ካራካስ፣ የአለማችን የቆነጃጅት ከተማ ለመባል በቅታለች፡፡
የታይላንዷ መዲና ባንኮግ በ7 የአለማቀፍ የቁንጅና ውድድሮች አሸናፊ ቆነጃጅት የሁለተኛነት ደረጃን ስትይዝ፣ የአውስትራሊያዋ ሲድኒ እና የፊንላንዷ ጥንታዊት ከተማ ቱርኩ በተመሳሳይ በስድስት ባለዘውድ ቆነጃጅቶቻቸው ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
የፊሊፒንስ መዲና ማኒላ፣ የፖርቶ ሪኮ መዲና ሳን ጁኣን፣ የቬንዙዌላዋ ማራቺያቦ እያንዳንዳቸው በተመሳሳይ በአምስት ተሸላሚ ቆነጃጅት አራተኛ ደረጃን እንደያዙ የጠቆመው ዘገባው፣ ባርሴሎና፣ ጁሃንስበርግ፣ ሪዮ ዲ ጄኔሮና ሳኦ ፖሎ እንዲሁም ቫለንሺያ በተመሳሳይ አራት ቆነጃጅት አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።


Read 5356 times