Print this page
Wednesday, 27 October 2021 00:00

“ስሙ የጠፋው” ፌስቡክ ስሙን ሊቀይር ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 በንግድ ምልክቱና በገበያ ዘንድ ባለው ገጽታ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማድረግ የተዘጋጀው ታዋቂው ማህበራዊ ድረገጽ ፌስቡክ፣ ከቀናት በኋላ ስያሜውን ሊቀይር ማሰቡን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በአለማቀፍ ደረጃ የተዛቡ መረጃዎችን በማሰራጨት፣ ለግጭትና ብጥብጥ መፋጠን ሰበብ በመሆንና የተጠቃሚዎቹን ግላዊ መረጃ አሳልፎ በመስጠት የሚወቀሰውና መልካም ስምና ዝናው እየጎደፈ የሚገኘው ፌስቡክ፣ ይህን ገጽታውን ለመቀየር በማሰብ በመጪው ሳምንት በሚያካሂደው አመታዊ ጉባኤው ስሙን ለመቀየር ማቀዱን የጠቆመው ዘገባው፣ ለራሱ ሊያወጣ ያሰበው ስም ምን የሚል እንደሆነ ግን ለጊዜው የታወቀ ነገር እንደሌለ አመልክቷል፡፡
ኩባንያው ምናልባትም በስሩ የሚያስተዳድራቸውን ፌስቡክ፣ ዋትሳፕና ኢንስታግራም አፕሊኬሽኖች በአንድ ኩባንያ ጥላ ስር በማዋቀር አዲስ ስያሜ ሊያወጣ እንደሚችል የተነገረ ሲሆን፣ የስያሜ ለውጡ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ይህ ነው የሚባል ለውጥ ያመጣል ተብሎ እንደማይጠበቅም ዘገባው አስረድቷል፡፡

Read 2782 times
Administrator

Latest from Administrator