Saturday, 23 October 2021 12:37

“ቶማስ ሳንካራ አጭር የፖለቲካ ህይወት” መጽሀፍ ለንባብ በቃ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

  በደራሲና ተርጓሚ ሰለሞን ዳኜ የተሰናዳውና በእውቁ አፍሪካዊ ፖለቲከኛና መሪ ቶማስ ሳንካራ ህይወትና ስራ ላይ የሚያጠነጥነው “ቶማስ ሳንካራ አጭር የፖለቲካ ህይወት ታሪክ” የተሰኘው መጽሐፍ ለንባብ በቃ።
“በዙሪያዬ ያሉትን  ሁሉ አንዱ  የቤተሰባችንን አካል በታሪክ አጋጣሚ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት በመሆኑ የተነሳ የተለየ ጥቅም ለማግኘት እንዳያስ አስተምሬያቸዋለሁ። ያላችው ንብረት ምንም ይን ምንም ሊያገኙት የሚገባው ሰርተውና ለፍተው እንጂ የፕሬዚዳንቱ ቤተሰብ በመሆናቸው መሆን የለበትም። ሚስቴም ትሁን እህት ወንድሞቼ አለያም ወደ ፊት የሚያድጉት ልጆቼ በኔ ስልጣን የተነሳ የተለየ ጥቅም ሊያገኙ አይገባም” በሚለው አይረሴ ንግግሩና አስተሳሰቡ ሁሌም የሚታወሰውና “አፍሪካዊው ቺጉ ቬራ” በመባል የሚታወቀው ቶማስ ሳንካራ የህይወት ታሪክ የፖለቲካ እንቅስቃሴውና አጠቃላይ ህይወቱ የተቋጨበት መንገድ በመጽሐፉ መዳሰሱም ታውቋል።
በተለያዩ ንዑስ ርዕሶች ተከፋፍሎ በ156 ገጽ የተቀነበበው መፅሐፉ በ170 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል። የመጽሀፉ አሰናጅ ሰለሞን ዳኜ ከዚህ ቀደም የእውቁን አፍሪካዊ የስነጽሁፍ ሰው ቺኖ አቸቤን “Things Fall a Part” የተሰኘ ትልቅ ስራ “ለየቅል” በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ መልሶ ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም።

Read 13444 times