Print this page
Saturday, 16 October 2021 00:00

የኢትዮጵያና ቱርክ የወታደራዊ ድሮን ሽያጭ ስምምነትን ግብጽ ተቃወመች

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(3 votes)

ቱርክ ለኢትዮጵያ ለመሸጥ የተስማማችውን “ባይራክተር ቲቢ 2” የተሰኘውን ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ሽያጭ ስምምነት ግብፅ አጥብቃ ተቃወመች።
 ሽያጩ እንዳይፈፀም አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ጣልቃ እንዲገቡ ግብፅ ጠይቃለች፡፡
ኢትዮጵያ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውለውንና “ባይራክተር ቲቢ 2” የተሰኘሰው አልባ አውሮፕላን ከቱርክ ለመግዛት ጥያቄ አቅርባ ጥያቄው ተቀባይነት በማግኘቱ ድሮኑን ለመረከብ በዝግጅት ላይ ስትሆን ግብፅ “የሽያጭ ስምምነቱ ተግባራዊ ሊሆን አይገባውም” ስትል ተቃውማለች፡፡ “ቱርክ ከኢትዮጵያ ጋር የትኛውንም አይነት ስምምነት ከማድረጓ በፊት ግብፅና ቱርክ በጉዳዩ ላይ መምከር ይኖርባቸዋል” ያለችው ግብፅ፤ ስምምነቱ ከመፈፀሙ በፊትና ኢትዮጵያ ድሮኖቹን ከመረከቧ አስቀድሞ አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ጣልቃ ገብተው ሊያስቆሙት ይገባል ብላለች-ግብፅ፡፡
ሞሮኮ ሰሞኑን የተረከበችው ኢትዮጵያ ግዥ ለመፈፀም የተስማማችው ቱርክ ሰራሹ ባይራክተር ቲቢ 2 የተሰኘው ወታደራዊ ሰው አልባ አውሮፕላን እስከ 150 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሮኬት፣ ቦምብና ሚሳየል በመሸከም፣ በ300 ኪሎ ሜትር ውስጥ ድሮኑን በመቆጣጠር ተልዕኮ ለማስፈፀም የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡


Read 9971 times