Saturday, 16 October 2021 00:00

ኢተዮ ቴሌኮም በ22 ከተሞች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ጀመረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ኢትዮ-ቴሌኮም ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታይባቸው የሀገራችን ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ለማስፋፋት በያዘው ስትራቴጂዊ ዕቅድ መሰረት የመጀመሪያውን ዙር የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ስራውን በ92 ከተሞች አጠናቆ አገልግሎት ማስጀመሩ ይታወሳል።
የመጀመሪያ ዙር የማስፋፊያ ሥራ በተጠናቀቀበት ወቅት እንደተገለጸው፣ በ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ መሰረት በ2ኛው ዙር የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ማስፋፊያ ተጠቃሚ የሚሆኑ ከተሞች የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የተለዩ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ.ም በ22 ከተሞች ማለትም በደደር፣ ዱብቲ፣ ደባርቅ፣ እስቴ፣ ሸሃዲ፣ ወረታ፣ ጃዊ፣ አዴት፣ ቢቸና፣ ደጀን፣ ሞጣ፣ አሰላ፣ ጎባ፣ ሮቤ፣ ሶደሬ፣ ባቱ፣ ሃላባ፣ ዱራሜ፣ ኮንሶ፣ ሳውላ፣ ሺንሺቾ  እና ወራቤ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎትን ማስጀመሩን ኩባንያው ገልጿል። በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ተጠቃሚ የሀገራችን ከተሞች ብዛት 114 ደርሷል ተብሏል። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ከሆኑ ከተሞች መካከል በ10ሩ (በደሴ፣ ደብረ ታቦር፣ ጎንደር፣ ባሕር ዳር እና ደብረ ማርቆስ ሎጊያ፣ ሆሳህና፣ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ቡታጅራ) ተጨማሪ የማስፋፊያ ሥራ ተጠናቆ አገልግሎት ላይ  መዋሉን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታውቋል።



Read 866 times