Sunday, 03 October 2021 00:00

የባቢሎን ስኬት እንጂ ውድቀት በኛ እንዳይደርስ!

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የባቢሎን ቋንቋ የተበተነው ወደኛ ነው?

“ምድርም ሁሉ፣ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች። ከምስራቅም ተነስተው በሄዱ ጊዜ፣ በሰናዖር ድምር፣ አንድ ሜዳ አገኙ። በዚያም ተቀመጡ። እርስበርሳቸውም፣ ኑ ጠብ እንስራ፤ በእሳትም እንተኩሰው ተባባሉ። ጠቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው።”…
ትረካው፤ በዚህች አጭር ገለፃ፣ የጥንቱን ታሪክ ይዘጋል። የአዲስ ታሪክ መነሻ እርሾም ይዟል- የታሪክ ችግኝ።
የባቢሎን የስኬት ታሪክ፣ ከአዲስ እውቀትና ሃሳብ በመነሳት፣ በአዲስ የአላማ እቅድ፣ ወደ አዲስ የአኗኗር ታሪክ የሚያሸጋግር ትረካ ነው። እንዴት?
ከባቢሎን በፊት፣ ታሪክ ሳይፈጠር
በፊት ነበረው ታሪክ፤ ብዙ ሺ ዓመታትን ቢያስቆጥርም እንኳ፤ ብዙ ትረካ የለውም። አነሳስና አወዳደቅ፣ ስኬትና ጥፋት፣ ቅርስና ጠባሳ ተብሎ የሚዘረዘር ብዙ ታሪክ ያልተፈጠረበት ዘመን ነው- የጥንቱ ዘመን።
ወፍ ዘራሽ ቅጠላ ቅጠልን እየበጠሰ፣ ስራስርን እየማሰ፣ ፍራፍሬዎችን እንደልብ እየሸመጠጠ፣… ከተቸገረም እየቃረመና እየለቀመ ይበላል። ከቻለ እንስሳትን ያጠምዳል። ወንዝ ወርዶ ይጠጣል። ዛፍ ስር ይጠለላል። ዋሻ ውስጥ ይተኛል፤ ይሸሸጋል።
ወቅቱ ሲለዋወጥ፣ ጎርፍ ሲንር፣ ዝናብ ሲጠፋ፣ መሬቱ ሲሰነጣጠቅ፣ ሳር ቅጠሉን ድርቅ ሲመታው፣… የድሮ ሰዎች መፍትሄ የላቸውም። ወደሌላ አካባቢ መፍለስ፣ ከተራራው ጀርባ፣ ከሸለቆው ማዶ ተሻግረው እድላቸውን ይሞክራሉ። የሚበሉት የሚጠጡት ነገር ካገኙ፣ ፍራፍሬና ቅጠላ ቅጠል፣ ምንጭና ወንዝ፣ መደበቂያና መጠለያ፣ ተራራና ዋሻ ካገኙ፣ መኖሪያቸው ይሆናል።
ነገር ግን፣ የያኔ “መኖሪያ”፣ ለጊዜው ብቻ ነው። መቆያ ነው። ከወቅት ፍርርቆሽ ጋር፣ መኖሪቸውን ይቀይራሉ። እንስሳትን ማላመድና ማርባት ከመጀመሩም በኋላ፣ አኗኗራቸው አልሰከነም። ግጦሽና ውሃ ፍለጋ ይጓዛሉ። ከተቀናቃኝ ከአጥቂ ይሸሻሉ።
የተቀናቃኝን ከብት ለመዝረፍ ይዘምታሉ። በአነስተኛ ቡድን ወይም በጎሳ፣ ከቦታ ቦታ እየተጓዙ፣ በዋሻ በጊዜያዊ መቆያ ውስጥ እየተጠለሉ ነው- የያኔው ኑሮ።
በሚቀጥለው ዓመት የሚቀጥለከው ክረምት- ዋሻው ባዶ ነው። የቅርስ ወይም የጠባሳ ምልክት አይኖርም። አሻራቸው የለም። ወደ ሌላ ቦታ ሄደዋል፤ ወይም ልጆቻቸውን ትተው ከዚህ ዓለም ተለይተዋል።
በቃ፤ ይሄው ነው። ከትውልድ ትውልድ ይደጋገማል። ሌላ የአኗኗር ዘዴና የሕይወት ዋስትና አልነበረም። ለዚህም ነው፤ በጥንታዊ መጻህፍት ውስጥ፣ የዘላንነት አኗኗርና የእንስሳት እርባታ በትልቅ ክብር የሚጠቀሰው። የእርሻ፣ የሸክላና የብረታብረት ሥራ ደግሞ፣ በበጎ አይን አይታይም። በተለይ የከተማ አኗኗር፣ ለረዥም ዓመታት በጥላቻ ይታይ ነበር። የአዳም ልጆችን አስታውሱ። አንዱ የተባረከ፣ ሌላው የተረገመ።
አቤል፣ እንስሳት አርቢ እረኛ ነው- የበግ መሥዋዕት ያቀርባል። ቃየን ግን፣ አራሽ ነው። የምድር ፍሬ ይዞ መጣ። ምድርን ባረሰህ ጊዜ፣ ንፉግ ትሆንብሃለች ተብሎ ተረግሟል። የእርሻ ሥራብቻ ሳይሆን፣ የብረታ ብረትና የሸክላ ስራ፣ ከዚህም ጋር የከተማ አኗኗር የተጀመረው በቃየን ትውልድ እንደሆነ ተተርኳል።
ታዲያ፣ ይሄ ሁሉ፣ ከቃየን ሃጥያት ጋር ተያይዞ ነው የተተረከው። የቃየን ሃጥያት፣ አቤልን መግደሉ ብቻ አይደለም። የአቤል የእንስሳት እርባታና የዘላንነት አኗኗርን “የሚገድል” አዲስ አኗኗር የመጣው በቃየን በኩል ነው። እርሻ፣ ድንኳን፣ ከተማ… እነዚህ ሁሉ፣ ከእርግማን ጋር የተዳበሉ፣ ከቃየን የፈለቁ ናቸው።
በአጭሩ፣ በመጀመሪያዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ትረካዎች ውስጥ፣ እርሻና ሸክላ፣ ብረትና ከተማ፣ በገናና ወይን፣… በጥሩ አይጠቀሱም።
የታሪክ ዋዜማ- እርሻና ወይን ጠጅ
ከጎርፍ ጥፋት በኋላ፣ የዛሬ 5000 ዓመት ገደማ ነው፤ የእርሻ ሥራና ኑሮ በበጎ የተነሳው። ኖህ ወደ እርሻ ስራ ገባ። “የድህረ ጎርፍ አዲስ ታሪክ “መሆኑ ነው- አዲስ የአኗኗር ታሪክ ዋዜማ።
ታዲያ፤ እንከን አላጣውም። አዎ፤ ስኬት ነው። ለእለት ጉርስ፣ ለአመት አስቤዛ ብቻ ሳይሆን፣ ከዚያ ያለፈና የተትረፈረፈ ምርት አግኝቷል- ከእርሻ።
ነገር ግን፣ ገና ከድንኳን ኑሮ አልተላቀቀም። ሌላም ነገር አለ። ከወይን ምርቱ፣ ወይን ጠጅ ጠምቆ ጠጣ። ጠጥቶም ሰከረ። በስካር መንፈስም፣ እርቃኑን አጋለጠ።
ማምረትና መፈብረክ አንድ ቁም ነገር ነው። ነገር ግን፣ ከዚህ ጋር አብሮ፣ ምርትን አሳምሮ በልኩ የመጠቀምና የማጣጣም ጥበብም ያስፈልጋል። አለበለዚያ፣ አናት ላይ ይወጣል፤ የሚያደርጉትን ያሳጣል። ለአዲሱ የእርሻ አኗኗር፣ ተስማሚ መላና ልክ ለማበጀት፣ ተጨማሪ ጥበብና ልምድ ከየት ይምጣ? ጊዜ ይፈጃል። ከትውልድ ወደ ትውልድ፣ ጥበብና ልምድ የሚያደረጁ ብልሆች ይመጡ ይሆናል። ግን ደግሞ፣ በመጠጥና በስካር እየተማረከ መረን የሚወጣ የጋጠወጥነት ትውልድ ሊበረክትም እንደሚችል ትረካው ይጠቅሳል። አንዱ የኖህ ልጅ ስለ አባቱ ስካር ወሬ እየነዛ እርግማን ወርዶበት የለ?
ለቴክኖሎጂና ለከተማ የሚመጥኑ፣ የእውቀት፣ የስነምርባርና የሕይወት መርሆች።
በዚህ ተባለ በዚያ፣ ለጥፋትም ለልማትም፣ የአዲስ ታሪክ ዋዜማው፣ ወደ መባቻው መሸጋገሩ አልቀረም- ከነአደጋው።
ከዋሻ ወደ እርሻ፣ ከድንኳን ወደ ከተማ ነው ጉዞው። ግን፣ ችግሮች አሉት።
አዎ፤ ጉዞው፣ የስልጣኔና የብልፅግና እመርታ ነው። ግን በዚያው ልክ፣ የግል የማንነትና የሃላፊነት እመርታን ይጠይቃል።
ስልጣኔ፣ ስልጡንነትን ይጠይቃል። ብልጽግና የሰብዕና ብቃትን ይሻል። ቴክኖሎጂና ከተማ፣ ጎን ለጎን የእውቀትና የስነምግባር ብቃት ያስፈልገዋል።
ለመኪና የማይመጥን አሽከርካሪ ሞልቶ የለ። በዚህም ሳቢያ ብዙ ሰው ይሞታል። ለድምጽ ማጉያ የማይመጥኑ ሰዎችም ጥቂት አይደሉም። ልብን የሚያደልቅ ግድግዳውን የሚያንቀጠቅጥ ዘፈን እያስጮኸ መንደር ይረብሻል። ከሬድዮ እስከ ኢንተርኔት ቴክኖሎጂው በሽ ሆኗል። ነገር ግን፣ ለቴክኖሎጂው የማይመጥኑ ሰዎች ሞልተዋል። እንቶ ፈንቶ የሚያወሩ፣ የጥላቻ ቅዠት እየተራጩ፣ በየፊናቸው በእልፍ አቅጣጫ አገርን የሚንጡ፣ በየቀኑ ይፈለፈላሉ።
የአቅጣጫና የፍጥነት መቆጣጠሪያ የላቸውም። እውነትና እውቀት፣ ጥሩና መጥፎ፣ መልካምና ክፉ፣ ነጻነትና ወንጀል፣ ጀግናና ወራዳ፣ ጨዋና ባለጌ… የሚሉ የሃሳብና የንግግር፣ የተግባርና የባሕርይ… በአጠቃላይ የስምግባርና የሕይወት መርህ የላቸውም።
መልክም ልክም የሌለው፤ የዘፈቀደና የተዘበራረቀ የቅዠት አለም ይመስላል- ነገረ ስራቸው። ይሄ መርህ አልባ የቅዠት ቅብዝብዝነት፣ አዲስ አይደለም። በባቢሎን ዘመን ታይቷል። ዛሬም በሰፊው ይታያል- እጅጉን እየተንሰራፋ ከቀን ወደቀንም እየጦዘ።
መርህ አልባ ቅዠት፣ ከስልጣኔ፣ ከቴክኖሎጂና ከከተማ ጋር አያዛልቅም። ወደ ጥፋትና ወደ ትርምስ ነው የሚያመራው። ለከተማ አኗኗር አይመጥንም።
ድሮ በጥንቱ በጥዋቱ፣ ከታሪክና ከስልጣኔ ዋዜማ በፊት፣ የዘፈቀደ የተዘበራረቀ ነገር አልነበረም። የጥንት ሰዎች፣ እውቀትና መርህ ባይኖራቸውም፣ ያን ያህል ችግር አይፈጥርባቸው። በትንሽ ቡድን፣ በትንሽ መንደር ነው፣ እድሜ ልካቸውን የሚያሳልፉት። እያንዳንዱ ሰው፣ ይተዋወቃል።
በክፉም በደጉም፣ ብዙ ጊዜ ተሞካክሮ ተፈታትሾ፣ መልኩና ልኩን በተግባር ተያይቷል። የመከባበር መርህ ባይኖራቸውም፣ ተደባድበው ትግል ገጥመው፣ ማን እንደሚያሸንፍ ተለይቶ ነው፤ የሰላምና የመከባበር ቅደም ተከተል ላይ የሚደርሱት።
በእውቀትና በመርህ ባይሆንም፣ ምን የተፈቀደ፣ ምን የተከለከለ እንደሆነ፣ እያንዳንዱ የመንደሩ ሰው ይገባዋል። ውዝግብ የለም። በትዕዛዝና በግዴታ፣ ተገርፎም ተመክሮም ተላምዷል- ተግባርና አኳሃን፣ ንግግርና አነጋገር ሁሉ ተወቅሮበታል- ቢያምንበትም ባያምንበትም። ሁሉም ነገር ከትዕዛዝ ጋር በቅጣትና በልማድ ነው። እናት ለልጇ ምጥ ታስተምራለች። ሌላ አማራጭ የለም። አለመግባባትም የለም። እያንዳንዱ መንደር የራሱ ዓለም ነው።
የመንደሩ ሰዎች፣ ይተዋወቃሉ፤ ይግባባሉ። ይህንም ለመግለጽ ይመስላል፤
“ምድርም ሁሉ፣ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች” ይላል ትረካው። በቡድን ይጓዛሉ፣ ይነጋገራሉ፣ ይግባባሉ።
“ከምስራቅም ተነስተው በሄዱ ጊዜ፣ በሰናዖር ምርድ፣ አንድ ሜዳ አገኙ። በዝያም ተቀመጡ።”
እርስ በርሳቸውም፤ “ኑ፣ ጠብ እንስራ፣ በእሳትም እንተኩሰው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው። የምድር ዝፍት፤ እንደ ጭቃ ሆነላቸው።…
በማለት ትረካው ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ይደርሳል። (ዝፍት፣ አስፋልት ለመስራት እንደሚውለው “ሬንጅ” ቁጠሩት)።
ከዚያስ?
የጡብ (የሸክላ) ስራ፣ አዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ነው። የቴክኖሎጂ ነገር፤ ብዙ ነው ቅርንጫፍና መልኩ። ስራን ያበረክታል- እንደማባዣ ነው። ያፈጥናል። ጉልበት ይጨምራል። ይህም ብቻ አይደለም። የማይቻል የነበረ ነገር ለመስራት፣ አዲስ እድል ይከፍታል። እናም አዲስ ሃሳብ መጣ።
“ኑ፣ ለኛ ከተማ እንስራ፣ አናቱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንስራ። በምድር ላይ ሳንበተንም፤ ስማችንን እናስጠራው” አሉ።
ድሮ፣ እንደዚህ አይነት ነገር ተሰምቶም ተሞክሮም አያውቅም። ከቴክኖሎጂና ከከተማ በፊት፣ የሰዎች ሃሳብና ተግባር፣ ውሎና አዳር፣ ከምድር ጋር የተጣበቀ ነበር። በውንም በህልምም፣ ለክፉም ለደጉም፣ ከምድር የሚያላቅቅ፣ ከፍ ዝቅ የሚያሰኝ እድል አልነበረም። ወደ ከፍታ የማደግ ታሪክ አይፈጠርም።
ቅርስ አይተርፈውም።
ግን ደግሞ ወድቆ የመፈጥፈጥ አደጋና ጠባሳ አይገጥማቸውም ነበር። ንብረት ማፍራት ከሌለ፣ ንብረት ማጣት አይኖርም። አሁን ግን፣ “የኛ” የሚሉት ቋሚ መኖሪያ ለመስራት አለሙ። በዚያ ላይ፤ ሰማይ ጠቀስ ግንብ መስራት አማራቸው፤ ቴክኖሎጂው ተፈጥሯላ።
ምንም አይጠረጠርም። ሰው፣ ሃሳብና አላማ ከያዘ፤ ሃላፊነት ከወሰደና ከሰራ፤ ወደ ስኬትና ወደ ከፍታ ይጓዛል። ቴክኖሎጂ እና ከተማ ደግሞ፣ የስኬት ውጤት የመሆናቸው ያህል፤ ለላቀ ስኬትና ከፍታ ያንደረድራሉ። የሰውን አቅም በብዙ እጥፍ ይበዛሉ፤ ያፈጥናሉ።
እውነትም፤ በሰው ልጅ የህልውና ዘመናት ውስጥ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ፤ አዲስ የሚጨበጥ ታሪክ ተሰራ ለቅርስ የሚተርፍ አዲስ ከፍታ ተገነባ።
የባቢሎን ጠቢባን፣ አስበውና ተናግረው አልቀሩም። ያሰቡትን ሰርተዋል፤ ያለሙትን ገንብተዋል። ስመ ጥሩዋና ገናናዋ ባቢሎን ተወለደች።
በ50ሺ ዐመታት የሰው ልጅ ህልውና ውስጥ፣ ታይቶ የማይታወቅ ነገር ተፈጠረ። “የሰው ልጅ ታሪክ ተጀመረ” ብንል፤ እንደ ማጋነን አይቆጠርም።
አዲስ አለም፣ አዲስ ሰው ከመፍጠር ይተናነሳል?
ኮከቦች ሲገጣጠሙ- ቴክኖሎጂ፣ ከተማ፣ ኢንተርኔት።
ችግሩ ምንድነው፤ በአዲስ አለም፣ በአዲስ መሳሪያና በአዲስ ከፍታ ላይ ሆኖ፣ እንደ ድሮው መቀጠል የሚችል ይመስለዋል ብዙ ሰው።
የእርሻው ፍሬ በርክቶለታል። ግን፣ መልክና ልኩን ካላወቀ መስከርና መዋረድ አለ።
ተባብሮ ለመስራት ይመቻል፣ ያበለጽጋል ቴክኖሎጂ። ነገር ግን ለመደባደብም ይውላል። በባዶ እጅ ወይም በዱላ መደባደብ ለምዶ፣ የጦርና የጎራዴ ቴክኖሎጂ ከታጠቀ በኋላም፣ እንደ ዋዛ መደባደብ ቢያምረው አስቡት። ሽጉጥና ጠመንጃ ላይ ሲደርስ አስቡት። በእሩምታ ደርዘን ሰዎችን የሚያጭድ ክላሽንኮቭ፣ በአንድ ፍንዳታ ቤተሰቡን ሁሉ የሚፈጅ ቦምብ፣ በመላው አገር በመላው አለም ሲትረፈረፍ ይታያችሁ።
በዱላና በድንጋይ ከመፈነካከት ጋር አነፃፅሩት። እነ መድፍ እነ ሚሳኤል በገፍ ሲታከሉበትማ፣ አደጋው እልቂት ነው።
በእርግጥ፣ አብዛኛው ሰው በየተራራውና በየሸለቆው ተበታትኖ የሚኖር ከሆነ፤ አደጋው ይቀንሳል። ታጣቂና ዘማች የሚበረክተው፤ ኢላማና ሟች በገፍ የሚበዛው፤ ከተሞች ሲስፋፉ ነው።
እንዲያም ሆኖ፣ እርስ በርስ የመነጋገርና የመገናኘት እድል እንደ ልብ ካልተትረፈረፈ በቀር፣ አለመግባባትን የማራባትና ውዝግብን የማራገብ፣ ጥላቻን የማቀጣጠልና መጠፋፋትን የመቀስቀስ እድል ይቀንሳል።
የተራራቀና የተበታተነ የገጠር አኗኗር ውስጥ፣ እውነትም ሆነ ሀሰት፣ ለብዙ ሰው በፍጥነት ማሰራጨትና ማናፈስ ይከብዳል። እውቀትንም ሆነ ጭፍን እምነትን የማስፋፋትና የማዛመት፣ አላማ በገጠር አኗኗር ያስቸግራል። መከባበርን ወይም ፀብን የመኮትኮትና የማቀጣጠል፤ ለስራ ወይም ለመጠፋፋት የማነሳሳት ህልምና ጥማት በቀላሉ አይሳካም።
ለእድገት የማስቸገሩ ያህል ለጥፋትም ያስቸግራል-የተበታተነ የተራራቀ የጥንት አኗኗር። ብዙ መገናኘትና መነጋገር የለም -ለነገር ፍለጋም፣ ለቁም ነገርም።
ከተማ ግን፣ ብዙዎችን ያገናኛል። ሬድዮና ቲቪ፣ ኢንተርኔትና ሞባይል ደግሞ፤ ቀን ከሌት እያገናኘ እልፍ አእላፍ ነገር ያናግራል።
ይሄኔ፣ ለቁም ነገር ከሆነ፤ በረከት ነው፤ ሲሳይ ነው። ለነገር ፍለጋ ሲሆን ደግሞ፤ አደጋው ታይቶ የማይታወቅ መዐት ነው።
ካሁን ቀደም፣ በሰው የህልውና ዘመናት ውስጥ፣ እንደ ዛሬ አይነት ሚሊዮኖችን የሚያገናኝና ጥዋት ማታ ለፀብ የሚያናግር ቴክኖሎጂ ታይቶ አይታወቅም። አዲስ ታሪክ ነው። ለቁም ነግር ሲውል፣ ድንቅ ታሪክ ነው፤ በዚያው መጠን አደገኛ።
የዛሬው ድንቅ ዘመን፤ ከባቢሎን ድንቅ ዘመን ጋር ይመሳሰላል። ታይቶ ከማይታወቅ አዲስ ፈጠራ ጋር፤ ታይቶ የማይታወቅ የትርምስ አደጋ ይፈጠራልና።
ይህን በቅጡና ከምር አለመገንዘብ፤ ከባቢሎን ታሪክ አለመማርና ታላቅ ጥፋትን መጋበዝ ይሆናል።
“ጌታም፣ የአዳም ልጆች የሰሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። ጌታም አለ፤ ”እነርሱ አንድ ወገን ናቸው። ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው። ይህንም ለማድረግ ጀመሩ። ያሰቡትን ሁሉ ለመስራትም አይከለከሉም። ኑ እንውረድ። አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን እንደባልቀው…’’
ይላል ትረካው።
ከተማ ሰርተዋል፤ ሰማይ ጠቀስ ህንፃ ገንብተዋል። የከተማ ስራ ግን አያልቅም። እየጨመረ እየፈጠነ ይሄዳል እንጂ። ግን ምን ዋጋ አለው። ከተማ ቢገነቡም፤ ለከተማ ኑሮ አልመጠኑም። መግባባት አቃታቸው። ብትንትናቸው ወጣ። ባቢሎን እንዳልተፈጠረች ሆና ጠፋች።

Read 1289 times