Tuesday, 21 September 2021 00:00

ሳን ፍራንሲስኮ ለኑሮ ምቹ የሆነች ቀዳሚዋ የአለማችን ከተማ ተባለች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 የአለማችንን ከተሞች በተለያዩ መስፈርቶች በመገምገም በየአመቱ የኑሮ አመቺነት ደረጃ የሚሰጠው ታይም አውት የተባለ ተቋም ከሰሞኑም የ2021 ሪፖርቱን ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ የአሜሪካዋ ሳን ፍራንሲስኮ ከአለማችን ከተሞች መካከል ለኑሮ እጅግ ምቹ የሆነች የአመቱ ከተማ ተብላ በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ተቋሙ በአለም ዙሪያ የሚገኙ ከ27 ሺህ በላይ ሰዎችን በማነጋገር  የሰራውን ጥናት መሰረት በማድረግ ባወጣው የአለማችን ከተሞች የኑሮ አመቺነት ሪፖርት፤ የሆላንዷ አምስተርዳም የሁለተኛ፣ የእንግሊዟ ማንችስተር ሶስተኛ ደረጃን መያዛቸውንም ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
የዴንማርኳ ኮፐንሃገን፣ የአሜሪካዋ ኒው ዮርክ፣ የካናዳዋ ሞንትሪያል፣ የቼክ ሪፐብሊኳ ፕራግ፣ የእስራኤሏ ቴል አቪቭ፣ የፖርቹጋሏ ፖርቶ እና የጃፓኗ ቶክዮ እንደ ቅደም ተከተላቸው ከአራተኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ መያዛቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡
የከተሞችን የኑሮ አመቺነት ሁኔታ ለመገምገም ከሚጠቀምባቸው መስፈርቶች መካከል የመሰረተ ልማት አውታሮች መስፋፋት፣ የመዝናኛ ተቋማት ሁኔታ፣ ለአካባቢ ጥበቃ የሚሰጠው ትኩረት፣ የመስተንግዶ ብቃት፣ ባህልና ኪነጥበብ፣ የሸቀጦችና አገልግሎቶች ዋጋ ወዘተ ይገኙበታል፡፡


Read 10941 times