Print this page
Saturday, 18 September 2021 16:41

እርዳታ ጭነው ትግራይ የገቡ 431 ተሽከርካሪዎች አልተመለሱም

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(1 Vote)

  የዓለም ምግብ ድርጅት እርዳታ ለማጓጓዝ የመኪና እጥረት ገጥሞኛል ብሏል
                    
              ከሐምሌ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የእርዳታ ቁሳቁሶችን  ጭነው ወደ ትግራይ ክልል ከገቡ 466 የጭነት ተሽከርካሪዎች መካከል የተመለሱት 38 ብቻ  መሆናቸውንና 431 ተሽከርካሪዎች የት እንደገቡ እንደማይታወቅ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡
ባለፈው ሳምንት ብቻ የእርዳታ ቁሳቁስ ጭነው መቀሌ ከደረሱ 149 ተሽከርካሪዎች መካከል አንዳቸውም አለመመለሳቸውን የመንግስታቱ ጽ/ቤት ገልጿል፡፡
የተሽርካሪዎቹ ከክልሉ አለመመለስ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረበት መሆኑን ያስታወቀው ድርጅቱ፤ ሁኔታው እጅግ አሳስቦኛል ብሏል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወደ ትግራይ ክልል የእርዳታ እህል ለማጓጓዝ የተከራያቸው እነዚህ የጭነት ተሽከርካሪዎች የት እንደገቡ እስካሁን ድረስ  የታወቀ ነገር አለመኖሩንና ሰብአዊ እርዳታ ወደ ክልሉ ለማድረስ የጭነት ተሽከርካሪዎቹ እንደሚያስፈልጉት ገልጿል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክረተሪያት ሀላፊ ቢልለኔ ስዩም ከትናንት በስቲያ በሰጡት መግለጫ፤ ትግራይ ክልል ከገቡ የጭነት ተሽከርካሪዎች መካከል 428 ያህሉ ከክልሉ አለመውጣታቸውን ተናግረው ነበር፡፡ እነዚህ ተሽከርካሪዎች በክልሉ ውስጥ በምን አገልግሎት ላይ እየዋሉ እንደሆነ ግልጽ ባለመሆኑ በመንግስት በኩል ጥርጣሬን አስከትሏል ብለዋል፡፡ የሰላም ሚኒስቴር  በበኩሉ፤ ከሳምነት በፊት አውጥቶ በነበረው መግለጫ፤ ወደ ትግራይ ክልል እርዳታ ጭነው የገቡ ተሽከርካሪዎች በተቀመጠው  ስርዓት መሰረት፤ ተመልሰው መውጣት ሲገባቸው እስካሁን አለመመላሳቸው አሳሳቢ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጿል፡፡

Read 11875 times