Monday, 06 September 2021 00:00

ቻይና ህጻናት በሳምንት ከ3 ሰዓት በላይ ጌም እንዳይጫወቱ ከለከለች

Written by 
Rate this item
(2 votes)

 የቻይና ህጻናት የኢንተርኔት ጌሞችን አዘውትረው በመጫወት ለተለያዩ ችግሮች እንዳይጋለጡ ለማድረግ ያቀደው የአገሪቱ መንግስት፣ ህጻናቱ በሳምንት በድምሩ ከ3 ሰዓታት በላይ መሰል ጌሞችን እንዳይጫወቱ የሚከለክል አዲስ ህግ ማውጣቱን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
የቻይና ብሔራዊ የፕሬስና ፐብሊኬሽን አስተዳደር ይፋ ያደረገውና ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ በስራ ላይ የዋለው ህግ እንደሚለው፣ ህጻናት የድረገጽ ጌሞችን መጫወት የሚችሉት አርብ፣ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በበዓል ቀናት ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
ከዚህ በፊት የወጣ ተመሳሳይ ህግ ህጻናቱ በየቀኑ ለአንድ ሰዓት ተኩል ጌም እንዲጫወቱ ይፈቅድ እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው፣ አዲሱ ጥብቅ ህግ በጌም ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ የአገሪቱ ኩባንያዎችን ክፉኛ ይጎዳል ተብሎ መሰጋቱን አመልክቷል፡፡

Read 2964 times