Saturday, 04 September 2021 13:22

“የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ” ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በቅርቡ አገርን ባስደመመውና ረጅም ሰዓት በወሰደው የልብ ቀዶ ህክምና አንድ የልብ ህመምተኛ ህጻንን በፈወሰው ወጣት የልብ ህክምና ባለሙያ ዶ/ር ፈቀደ አግዋር የተጻፈው “የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ” መጽሐፍ ዛሬ ከረፋዱ 3፡00 ጀምሮ በቀነኒሳ ሆቴል ይመረቃል፡፡
መፅሐፉ በዋናነት በሀገራችን የልብ ቀዶ ህክምና መስራት ከተጀመረበት አራት ዓመታት ወዲህ ዶክተሩ ከስራ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን 312 ያህል የልብ ቀዶ ህክምናዎችን በስኬት ያጠናቀቀ ሲሆን ከዘኒህም መካከል በቀዶ ህክምናው ሂደት ከፍተኛ ፈተና ሆነው የነበሩትን 17 ቀዶ ጥገናዎች መሰረት በማድረግ አጠቃላይ የልብ ህክምናዎችን  ውስብስብነትና ተያያዥ ነገሮችን ዳስሷል።
በምረቃው ሥነ-ስርዓቱ ላይ በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር)፣ ስንታየሁ ፀጋዬ (ዶ/ር) ደራሲና ጋዤጠኛ ተስፋዬ ማሞ የመፅሀፍ ዳሰሳ የሚያቀርቡ ሲሆን ታካሚዎች ስለ ልብ ህመምና ከህመሙ መዳን የሚሠጠውን ስሜት ያጋራሉ ተብሏል፡፡ የመፅሀፉ ደራሲ ዶ/ር ፈቀደም ስለ መጽሀፉና በአጠቃላይ የልብ ህክምና ዙሪያ ገለፃ እንደሚያደርጉም ታውቋል፡፡

Read 35040 times