Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 08 September 2012 12:55

የዙማ ስእል አወዛጋቢ ሆኗል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የደቡብ አፍሪካውን ፕሬዝዳንት የሚተች የቀለም ቅብ በአንድ ደቡብ አፍሪካዊ ሰዓሊ ተሰርቶ ለኤግዚብሽን መቅረቡ እያወዛገበና ተቃውሞ እያስከተለ መሆኑን የተለያዩ ዘገባዎች ጠቆሙ፡፡ በኬፕታውን በሚገኝ አንድ ጋለሪ ለእይታ የቀረበው ስዕሉ፤ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በዙሉ አለባበስ እና ዳንስ ሃፍረተ ስጋቸው እየታየ ሲጨፍሩ የሚያሳይ ነው፡፡ ዙማ የሚመሩት የኤኤንሲ ፓርቲ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ተቋማት ስእሉ ህገመንግስቱን የጣሰ፤ ግብረገብ የጎደለው ጋጠወጥ ተግባር በሚል እያወገዙት ሲሆን ፕሬዝዳንት ዙማ እንደ ግለሰብ፤ እንደ አባት እና እንደቤተሰብ ሃላፊ የሚገባቸውን ክብር የነፈገ በመሆኑ ሰዓሊው ሊቀጣ ይገባል እያሉ ናቸው፡፡ በኬፕታውን ‹አወር ፋዘርስ› በሚል በተዘጋጀ ኤግዚብሽን ላይ ለእይታ የቀረበው የቀለም ቅቡን የሳለው አርቲስት አያንዱ መላቡሊ የተባለ ሲሆን ርእሱን ‹ዌፐን ኦፍ ማስ ዲስትራክሽን› ብሎታል፡፡

ሰዓሊው በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተቃውሞ የተሰነዘረበትን ስራውን በመከላከል በሰጠው መግለጫ፤ ስእሉን የሰራሁት የደቡብ አፍሪካ ህዝብ በስንት መከራና ችግር እየተሰቃየ ጃኮብ ዙማ እንደመሪ ከመጨነቅ ይልቅ ቅንጡ ህይወትና ፌሽታ ማብዛታቸውን ለመተቸት የሰራሁት ነው ብሎ ተናግሯል፡፡በፖለቲካ እና በግል ህይወታቸው አወዛጋቢ ሆነው የቆዩት ጃኮብ ዙማ ስምንት ሚስቶች እና 20 ልጆች እንዳላቸው ይነገራል፡፡

 

 

Read 2152 times Last modified on Saturday, 08 September 2012 12:57