Saturday, 14 August 2021 13:38

በXXXII ኦሎምፒያድ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

  ከ32ኛው ኦሎምፒያድ በኋላ
ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው 14 ኦሎምፒያዶች (ሜልቦርን፤ ሮም፤ ቶኪዮ፤ ሜክሲኮ፤ ሙኒክ፤ ሞስኮ፤ ባርሴሎና፤ አትላንታ፤ ሲድኒ፤ አቴንስ፤ ቤጂንግ፤ ለንደን፤ ሪዮ ዲጄኔሮ እና ቶኪዮ) ላይ 234 ኦሎምፒያኖች የተሳተፉ ሲሆን 173 ወንድ 60 ሴት ናቸው፡፡
23 የወርቅ ሜዳልያዎችን 14 ኦሎምፒያኖች፤ 12 የብር ሜዳልያዎችን 11 ኦሎምፒያኖች እነዲሁም 23 የነሐስ ሜዳልያዎችን 20 ኦሎምፒያኖች ተጎናፅፈዋቸዋል፡፡
በሁለቱም ፆታዎች
23 የወርቅ 12 የብር 23 የነሐስ 58 ሜዳልያዎች
22 አራተኛ ደረጃ ፤ 9 አምስተኛ ደረጃ፤ 14 ስድስተኛ ደረጃ፤ 5 ሰባተኛ ደረጃ፤
7 ስምንተኛ ደረጃ
በሴቶች
10 የወርቅ 5 የብር 11 የነሐስ 26 ሜዳልያዎች
12 አራተኛ ደረጃ፤   5 አምስተኛ ደረጃ 2 ስድስተኛ ደረጃ 2 ሰባተኛ ደረጃ
2 ስምንተኛ ደረጃ
በወንዶች
13 የወርቅ 7 የብር 12 የነሐስ 32 ሜዳልያዎች
11 አራተኛ ደረጃ፤ 4 አምስተኛ ደረጃ፤ 12 ስድስተኛ ደረጃ ፤3 ሰባተኛ ደረጃ፤
5 ስምንተኛ ደረጃ
በ32ኛው ኦሎምፒያድ  ኢትዮጵያን በ4 ስፖርቶች በአትሌቲከስ፤ በውሃ ዋና፤ ብብስክሌትና በቴክዋንዶ የወከሉት  38 ኦሎምፒያኖችን  ነበሩ። 4 የኦሎምፒክ ሜዳሊያዎች (1 የወርቅ ፤ 1 የብርና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች) የተገኙ ሲሆን ሰለሞን ባረጋ በ10ሺ ሜትር የወርቅ፤ ለሜቻ ግርማ በ3ሺ መሰናክል የብር፤ ጉዳፍ ፀጋይ በ5ሺ ሜትር የነሐስ እንዲሁም ለተሰንበት ግደይ በ10ሺ ሜትር የነሐስ ሜዳልያዎችን አግኝተዋል፡፡ ብዙም ያልታወቀ ሽልማት ቢሆንም ከ4 እስከ ስምንተኛ ደረጃ  በማግኘት 11 ኦሎምፒያኖች  የኦሎምፒክ ዲፕሎማዎችን አግኝተዋል። 11 ኦሎምፒያኖች በየውድድር መደባቸው ማጣሪያዎችን ያለፉ ሲሆን 7 ኦሎምፒያኖች ውድድራቸውን አቋርጠው ወጥተዋል።
በኦሎምፒክ መድረክ ላይ ኢትዮጵያን በቴኳንዶ ስፖርት በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ወክሎ የተሳተፈው ሰለሞን ቱፋ የጃፓናኑን ሱዙኪ እና የቱኒዚያውን  ጀንዳዊቢ አሸንፎ ግማሽ ፍፃሜ ከገባ በኋላ በራሽያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተሳታፊው አርትማኖቭ ተርቶ በሰባተኛ ደረጃ ዲፕሎማ ለመሸለም በቅቷል፡፡ በመክፈቻው ስነስርዓት የኢትዮጵያን ባንዲራ ያነገበው አብድልመሊክ ሙክታር በ50 ሜትር ነፃ የውሃ ዋና በመጀመርያው ዙር ማጣርያ ከውድድር ውጭ ሆኖ 62ኛ ደረጃ አግኝቷል፡፡
ኬንያ በ10 ሜዳሊያዎች (4 የወርቅ፤ 4 የብርና ሁለት የነሐስ ) በማግኘት ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃ ከዓለም 19ኛ ደረጃ ይዛ ጨርሳለች፡፡ ኡጋንዳ 4 ሜዳልያዎች (2 የወርቅ፤ 1 የብርና 1 የነሐስ)፤ ደቡብ አፍሪካ 3 ሜዳልያዎች (1 የወርቅ፤ 2 የብር)  እንዲሁም ግብፅ 6 ሜዳልያዎች (1 የወርቅ፤ 1 የብርና 4 የነሐስ) ከኢትዮጵያ በላይ ባሉ ደረጃ የጨረሱ የአፍሪካ አገራት ናቸው፡፡

Read 1184 times