Wednesday, 04 August 2021 00:00

“ሒድ ና” ፊልም በስከላ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)


              በደራሲ የምስራች ታደለ ተደርሶ በአርቲስት ቢኒያም ሽፋ የተዘጋጀው “ሒድ ና” ፊልም ሀምሌ 18 ቀን 2013 ዓ.ም የአባይ መነሻ በሆነው ስከላ በድምቀት ተመረቀ።
ፊልሙ ከአባይ መነሻ ስከላ ጀምሮ የፊልምና የታሪክ ፍሰቱን ጠብቆ እስከ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የሚዘልቅ ኢትዮጵያዊያን በፍቅር አንድ የሚሆኑበት ታሪክና መቼት የያዘና አዝናኝ ፊልም ነው ተብሏል።
የ1፡40 ሰዓት ርዝመት ያለው ፊልሙ ቀረፃው በሰከላ፣ ፒኮሎ አባይ፣ አዲስ አበባ ቲሊሊ ባህርዳርና ሌሎችም የአባይ ገባር ወንዞች ያሉበት ቦታ ያደረገ ሲሆን በፊልሙ ላይ ካሳሁን ፍሰሀ (ማንዴላ) ችሮታው ከልካይ፣ የምስራች ታደለና ብሩክታዊት ሽመልስ የተሳተፉበት ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ፊልም መሆኑን የፊልሙ ዳይሬክተር አርቲስት ቢኒያም ሽፋ ገልጿል።



Read 920 times