Saturday, 07 August 2021 14:14

“የውሻ ፖለቲካ” መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በደራሲ ሙሉቀን ሰለሞን የተፃፈውና የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ የሆነው “የውሻ ፖለቲካ” መፅሐፍ ባሳለፍነው ሳምንት ለንባብ በቃ።
ደራሲው ዘመኑን የታዘበበትንና የተደመመባቸውን የተመረጡ 8 አጫጭር ታሪኮች በመፅሀፉ ያካተተ ሲሆን፣ ደራሲው ለየት ባለ የአጫጭር ልቦለድ አፃፃፍ ስልት መፅሐፉን ማቅረቡ እንዳስደሰተው “አውሮራ”፣ “የቄሳር እንባ”፣ “የሱፍ አበባ” እና “ታላቁ ተቃርኖ” በተሰኙ ድንቅ መፅሐፎች የምናውቀው ደራሲ ሀብታሙ አለባቸው በመፅሐፉ ጀርባ ባስቀመጠው ማስታወሻ ገልጿል። “የውሻ ፖለቲካ” መፅሐፍ የደራሲው ሁለተኛ ሥራ ሲሆን በ151 ገፅ ተቀንብቦ በ149 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል።
ደራሲው ከዚህ ቀደም “የወንበር ፍቅር” የተሰኘ የግጥም ስብስብ መፅሐፍ ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም።


Read 11328 times