Tuesday, 03 August 2021 18:29

“ነገረ ድርሰትና የአለማተ አማንያ ተረኮች” መፅፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  የኮተቤ ሜትሮዩቨርሲቲ መምህር በሆኑት በጎሰው የሺዋስ (ዶ/ር) ተሰናዳው “ነገረ ድርሰትና የዓለማተ አማንያን ተረኮች” መፅሀፍ ለንባብ የበቃ ሲሆን የዛሬ ሳምንት አራት ኪሎ በሚገኘው ኢክላስ ህንፃ ዛጎል መጻህፍት ባንክና ዋልስ መፅሀፍት በጋራ ባዘጋጁት ስነ-ስርዓት ቅዳሜ ነሀሴ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ይመረቃል።
መፅሀፉ በሁለት ክፍል የቀረበ ሲሆን በመጀመሪያው ክፍል፣ ስለድርሰት ምንነት፣ ስለልብወለድ ግጥም፣ ኢ-ልብወለድ አጻጻፍ  እንዲሁም ስለስንክሳር ገድል ምንነት የሚያትት ሲሆን፣ በሁተኛው ክፍል ደግሞ 11 ያህል እጅግ መሳጭ የአለማተ አማኒያንን ተረኮች ይዟል ተብሏል።
በ253 ገፅ የተቀነበበው ይህ መፅሀፍ በ180 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን፣ በምረቃው እለት ኮተቤ ዩኒቨርስቲ ምሁራን በመጽሀፉ ዙሪያ ጥናታዊ ጽሁፍ እንደሚቀርቡና በርካታ የስነ-ጽሁፍ ባለሙያዎችና የጥበብ አፍቃሪን እንደሚታደሙም ታውቋል።

Read 6620 times