Saturday, 24 July 2021 00:00

የአፍሪካ ህጻናት ቀንና “የአንድሮሜዳ ቁጥር ሁለት” መፅሐፍ ምረቃ ነገ በባህርዳር ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 የዘንድሮ የአፍሪካ ሕፃናት ቀንና “የአንድሮ ሜዳ ቁጥር 2” መፅሐፍ ምረቃ ነገ በባህርዳር አቫንገር ብሎ ናይል ሆቴል እንደሚካሄድ አዘጋጁ ሰምና ወርቅ ሚዲያና ፕሮሞሽን አስታወቀ።
በዕለቱ  ጥናታዊ የምርምር ስራ በመጋቤ ሀዲስ  ዶ/ር ሮዳስ ታደሰና ዶ/ር ጌትነት ፈለቀ የሚቀርብ ሲሆን በአዲስ አበባና በባህርዳር ያሉ ተመራማሪ የአንድሮ ሜዳ ህጻናት ይሳተፋሉም ተብሏል፡፡ በዚሁ ሥነ-ስርዓት ላይ “አንድሮሜዳ ቁጥር ሁለት” እና “የወርቅ ዘንግ” መፃህፍት የሚመረቁ ሲሆን በእውቅ ገጣሚያን ግጥም፣ በኢትዮጵያ የባህል ቡድን ምርጥ ኪነ- ጥበባዊ ዝግጅቶች፣ በስነ-ፈለክ መመልከቻ የሰማይ ምልከታ ሥነ-ስርዓት እንደሚከናወን የጠቆመው አዘጋጁ፣ በፕሮግራሙ ላይ ታዋቂ ግለሰቦች እንደሚታደሙ ተገልጿል፡፡

Read 12583 times