Saturday, 17 July 2021 14:42

የሳሚ ዳን “ስበት” አልበም በአዲስ ዓመት ዋዜማ ይለቀቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    ከትላንት በስቲያ ስራውን ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር ተፈራርሟል

          የእውቁ አቀንቃኝ ሳሙኤል ብርሃኑ (ሳሚ ዳን) ሶስተኛ ስራ የሆነው “ስበት” አልበም በአዲስ ዓመት ዋዜማ ለአድማጭ እንደሚደርስ ታወቀ፡፡ አርቲስቱ ከትላንት በስቲያ ሀምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ረፋድ ላይ በሳፋየር አዲስ ሆቴል የአልበሙን አጠቃላይ ህትመት የሙዚቃ ኮንሰርት፣ የሙዚቃ ቪዲዮ፣ የፕሮሞሽንና ተያያዥ ሥራዎችን ከሚሰራለት ከኖርዲክ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ./ማህበር ጋር ስምምነት ፈፅሟል፡፡
ቀደም ሲል ለአድማጭ ተመልካች ባደረሳቸው “ከራስ ጋር ንግግር” እና “አስራ አንዱ ገፆች” በተሰኙ አልበሞች እንዲሁም  በግልና በጋራ በሰራቸው ነጠላ ዜማዎች ተቀባይነትን ያገኘውና በርካታ ሽልማትን የተቀበለው ሳሚ ዳን፤ አሁን ደግሞ ላቅ  ባለ የሀሳብ ደረጃ፤ የቅንብርና ልዩ ፈጠራ የተሰናዳ የተባለለት አዲስ አልበም አጠናቋል፡፡  
የሙዚቃዎቹ ሀሳቦች ከልጅ እስከ አዋቂ የሚነኩ ሲሆን በተለይም ስለ ፍቅር፣ ስለመተሳሰብና አብሮነት የተቀነቀነ፣ በስልተ ምት ደረጃም ከፍታን የተላበሰ ነው ተብሎታል ይህ ደረጃውን የጠበቀና 13 ዘፈኖችን ያካተተ አልበም በጥራት ታትሞና ተዘጋጅቶ ለሙዚቃ አፍቃሪው በሚመጥን መልኩ እንዲደርስ ኖርዲክ ኃየተ/የግል ማህበር በሰለጠነና ልምድ ባለው የተዋቀረ ቡድን ሥራውን ሰርቶ ለመጨረስ በዕለቱ ቃል ገብቷል፡፡

Read 14595 times