Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 01 September 2012 12:07

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ህልፈተ ህይወት ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ተሰረዙ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕይወት ማለፍን ተከትሎ ብሔራዊ የሀዘን ጊዜ በመታወጁ በርካታ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ዝግጅቶች ተሰረዙ፡፡ ከተሰረዙት ዝግጅቶች መካከል የቴዎድሮስ ካሳሁን የአዲስ አመት ዋዜማ የሙዚቃ ድግስን ጨምሮ ፊልሞች፣ የትያትር መደበኛ ዝግጅቶች፣ የሙዚቃ ድግሶች እና የፋሽን ትርዒቶች ይገኙበታል፡፡ በዚሁ ብሔራዊ ሀዘን ምክንያት የመንግሥት ትያትር ቤቶች የትያትርና ፊልም እለታዊ ዝግጅቶችን የሰረዙ ሲሆን የግል ሲኒማ ቤቶችም የፊልም ምረቃዎችን ለሌላ ጊዜ አስተላልፈዋል፡፡ ለነገ ታስቦ የነበረው የ”ብርር…ር” ፊልም ምረቃ ለጳጉሜ 3፣ ለዛሬ ታስቦ የነበረው የኔክስት ዲዛይን ትምህርት ቤት የፋሽን ትርዒት ለመስከረም 5 ተላልፏል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የአቢሲኒያ የሥነ ጥበብ እና ሞዴሊንግ ማሰልጠኛ ተቋም ከትናንት ወዲያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር በከፈተው የሥዕል እና የቅርፃ ቅርፅ አውደ ርእይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስሎች ለእይታ ቀርበዋል፡፡ በዚሁ ዝግጅት ላይ የሀዘን መግለጫ መዝገብ ማዘጋጀቱን ትምህርት ቤቱ ጨምሮ ገልጿል፡፡

 

 

Read 1401 times Last modified on Saturday, 01 September 2012 12:08