Saturday, 19 June 2021 18:23

“ሰዎች እና ማህበራዊ ኑሮ” ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲ አማረ መልካሙ የተሰናዳውና በሰው ልጆች ማህበራዊ ኑሮና መስተጋብር ዙሪያ የሚያጠነጥነው “ሰዎች እና ማህበራዊ ኑሮ” መፅሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡መፅሐፉ በዋናነት የሰው ልጅ በተለያየ የአኗኗር ስርዓት በማለፉ ኢ-ፍትሃዊነት መንፈሱን መነሻ በማድረግ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ነፃነት፣ በነፃ ግብርናና ገበሬው፣ በንግድ ነፃነት ማጣትና መዘዙ፣ በሰውና በተፈጥሮ፣ በሰውና በስራ፣ በሙያና ሰው ዙሪያ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት ይተነትናል፡፡ በ214 ገፅ የተቀነበበው መፅሐፉ በ120 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን፣ በዋናነት ጃዕፈር መፅሐፍት መደብር እንደሚያከፋፍለውም ታውቋል፡፡


Read 12822 times