Saturday, 12 June 2021 12:56

ደራሲ ቃልኪዳን ሀይሉ አራተኛ ስራ “ክብር” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

በ2006 ዓ.ም “የነጎድጓድ ልጆች” የተሰኘ መፅሀፍ ለንባብ በማብቃት የድርሰቱን ዓለም የተቀላቀለው ደራሲ ቃልኪዳን ሀይሉ አራተኛ ሥራ የሆነው “ክብር” ልቦለድ መፅሀፍ ለንባብ በቃ፡፡ መቼቱን ኢትዮጵያና እንግሊዝ ላይ አድርጎ በፍቅር፣ በቅናት፣ በበቀልና በክብር ላይ ትኩረቱን ያደረገው መፅሀፉ፣ ክህደት ማታለል፣ ትዳር፣ ማፈንገጥና ሴራ ምን እንደሚመስሉ የሚያሳይና ራሳችንን እንድንጠይቅና እንድንፈትሽ የሚያደርገን ነው ተብሏል፡፡
በ148 ገፅ የተቀነበበው ይህ  መፅሀፍ በ120 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ደራሲ ቃልኪዳን ሀይሉ በማህበረሰብ ሳይንስ ከደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪውን፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በጋዜጠኝነትና ተግባቦት የማስተርስ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡
ደራሲው ከዚህ ቀደም “የነጎድጓድ ልጆች”፣ “ለምን አትቆጣም” ና “አላቲኖስ” የተሰኙ መፅፎች ለንባብ ማብቃቱ የሚታወስ ሲሆን “ዳና” እና “ወላፈን” በተሰኙ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በድርሰት ተሳትፎው አቅሙን ያሳየ ወጣት ደራሲ ነው፡፡

Read 3696 times