Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 18 August 2012 13:30

የብራድ ፒትና የአንጀሊና ሰርግ መቼ እንደሆነ አልታወቀም

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የብራድ ፒት እና የአንጀሊና ጆሊ የሠርግ ሥነ ስርዓት በደቡብ ፈረንሳይ ዛሬ እንደሚፈፀም ሲዘገብ ቢቆይም በመረጃው እርግጠኛ ለመሆን አለመቻሉን የተለያዩ ዘገባዎች አመለከቱ፡፡ ሁሉቱ የፊልም ተዋናዮች ላለፉት  ሰባት አመታት የቆዩበትን የፍቅር ግንኙነት ዛሬ በጋብቻ ያስሩታል ሲል በቅድሚያ የገለፀው “ሄሎ ማጋዚን” ነበር፡፡  ከትናንት በስቲያ ፒፕል መጋዚን የሠርግ ቀኑ እንደማይታወቅና ሰሞኑን በወጡ ዘገባዎች ስለጋብቻቸው በዛሬው ዕለት መሠረግ የተነገረው ሁሉ ሃሰተኛ መረጃዎች ናቸው ብሏል፡፡ “ፎክስ ኒውስ” ብራድ ፒት እና አንጀሊና ጆሊ ጋብቻቸውን እስከ 1 ሚሊዮን  ዶላር ባወጡባቸው ቀለበቶች ለመፈፀም መዘጋጀታቸውን ቢገልጽም የሰርጉ ቀን ግን መቼ እንደሚሆን የሚታወቅ ነገር እንደሌለ አመልክቷል፡፡ የሁለቱ እውቅ የሆሊውድ ዝነኞች ጋብቻ ዛሬ እንደሚሆን የገለፁ ዘገባዎች፤ በደቡብ ፈረንሳይ ቻቲዌ ሚርቫል በተባለ ስፍራ በሚገኝ ጥንታዊ ካስትል እንደሚከናወን ጠቁመው ነበር፡፡ የከተማዋ ከንቲባ ግን መረጃዎቹ ሃሰተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ከንቲባው ሁለቱን ዝነኞች ከእነጭራሹ አላውቃቸውም የሚል መግለጫቸ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ስለጉዳዩ መረጃ ለመጠየቅ ከ50 በላይ ስልኮች እንደተቀበሉና ለሁሉም         “ድራሻችሁ ይጥፋ” የሚል መልስ በቁጣ ሰጥተዋል፡፡

በሌላ በኩል ጄኒፈር አኒስተን ላለፈው አንድ አመት የፍቅር ጓደኛዋ ከነበረው ጀስቲን ቴሮክስ ጋር የቃልኪዳን ቀለበት ማሰሯን ፎክስ ኒውስ አስታውቋል፡፡ ተዋናይና ደራሲ የሆነው ጀስቲን ቴሬኮስ ለጄነፈር የጋብቻ ጥያቄ አቅርቦ ተቀባይነት እንዳገኘም ተገልጿል፡፡ የጄኒፈር አኒስተን አዲስ ትዳር የመመስረት ወሬ የቀድሞ ባሏ ብራድ ፒት ከአንጀሊና ጆሊ ጋር ጋብቻ ሊፈፅም በተቃረበበት የመጨረሻዋ ቅፅበት ላይ መሆኑ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል ተብሏል፡፡

ጄኒፈር አኒስተንና ብራድ ፒት ለአምስት አመት የዘለቀው ትዳርራቸውን ያፈረሱት 2005 እ.ኤ.አ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ብራድ ፒት ከዚህ ትዳሩ በኋላ ከአንጀሊና ጆሊ ጋር ፍቅር ሲጀምር አኒስተን ከሌሎቹ ታዋቂ ተዋናዮች ቪንስ ቮግዋንና ከጆን ሜየር ጋር ወጣ ገባ ስትል ቆይታለች፡፡

የ43 አመቷ ጄኒፈር አኒስተንና የ41 አመቱ ጀስቲን ቴሮክስ ለበርካታ አመታት በጓደኝነት መቆየታቸውን የገለፀው ፎክስ ኒውስ፤ ከአንድ አመት በፊት “ዎንደር ላስት” በተባለ ፊልም ላይ አብረው ከሰሩ በኋላ የፍቅር ግንኙነት መጀመራቸውን አስታውሷል፡፡

 

 

Read 1351 times Last modified on Saturday, 18 August 2012 13:32