በዋርነር ብሮስ 125 ሚሊዮን ዶላር በጀት ወጥቶበት የተሰራው “ዘ ቦርን ሌጋሲ” ከ “ዘ ዳርክ ናይት ራይዝስ” የሰሜን አሜሪካ ገበያን መንጠቁ ከፍተኛ ተወዳጅነት በማትረፉ ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡ ለእይታ ከበቃ ሶስት ሳምንት ያለፈው “ዘ ዳርክ ናይት ራይዝስ” በሰሜን አሜሪካ ገበያ አራት መቶ ሚሊዮን ዶላር በመላው አለም ደግሞ ስምንት መቶ ሚሊዮን ዶላር እንዳስገባ ታውቋል፡፡ ዋርነር ብሮስ ቀጣይ የቦርን ፊልሞችን በጄረሚ ሬነር ተዋናይነት “ኤ ቦርን ኢዝ ሪስታርትድ” እና “ቦርን ቱቢ ባድ” በሚሉ ርእሶች ለመስራት ይፈልጋል፡፡
በሌላ ዜና ማርቭል ስቱዲዮስ የ “ዘ አቬንጀርስ” ፊልምን የመጀመርያ ክፍል ለመስራት እና ለማስተዋወቅ 320 ሚሊዮን ዶላር ወጭ አድርጎ ገቢው በአለም ዙርያ ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ በመድረሱ ተከታዩን ፊልም ለመስራት እንዳነሳሳው ተገለፀ፡፡ የ “ዘ አቬንጀርስ” ፊልም በቦክስ ኦፊስ የገቢ ደረጃ ታሪክ 3ኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጠ ታውቋል፡፡ የፊልሙ ዲያሬክተርና ደራሲ ጆስ ዌደን ሁለተኛውን የ “ዘ አቬንጀርስ” ፊልም ለመስራት ጭብጡን እንደጠነሰሰ የገለፀው የኮንታክት ሚውዚክ ዘገባ ሲሆን ከሁለት አመት በኋላ ለእይታ እንደሚያበቃው መግለፁንም አውስቷል፡፡ ፊልሙን በሚቀጥለው አመት ላለመልቀቅ ማርቭል ስቱዲዮ የተገደደው በ “ዘ አቬንጀርስ” ላይ የሚሰሩ ሱፕር ሂሮዎች በራሳቸው ፊልሞች ሥራ በመጠመዳቸው ነው ተብሏል፡፡