Saturday, 27 March 2021 13:17

በእስር የምትገኘው አስቴር ስዩም “ሀገር ስታምጥ” መፅሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ያለፈውን ስርዓት በፅኑ ስትቃወምና በእስር ስታማቅቅ የነበረችውና አሁንም በእስር ላይ የምትገኘው ታጋይ አስቴር ስዩም (ቀለብ) በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሆና ያሳተመቸው “ሀገር ስታምጥ” መጽሐፍ ዛሬ መጋቢት 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል ይመረቃል።
በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰተረውና የታጋይ አስቴር ስዩምን የትግል ህይወት፣ የእስር ቤት ስቃይና ውጣ ውረዷን በሚያስቃኘው በዚህ መፅሀፍ ምርቃት ላይ የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ ማሙሸት አማረ፣ የባልደራስ ጽ/ቤት ሀላፊ ገለታው ዘለቀ፣ መምህርትና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ፣ አርቲስት አስቴር በዳኔ፣ የዩኒቨርሲቲ መምህሩ ሲሳይ መንግስቴ (ዶ/ር)፣ የታሪክ ምሁርና ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱና ሌሎችም አንጋፋና ወጣት እንግዶች በክብር ይገኛሉ ተብሏል።
በእለቱም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ፣ በመጽሐፉና በእስር ላይ ሰለምትገኘው ታጋይ አስቴር ስዩም ውይይት ይደረጋልም ተብሏል።

Read 10756 times Last modified on Saturday, 27 March 2021 13:35