ባለፈው ሳምንት ብቻ በአይስላንድ ባልተለመደ ሁኔታ እጅግ በርካታ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች መፈጠራቸውንና በሳምንቱ በአገሪቱ ደቡብ ምዕራባዊ ሪክጃኔስ ግዛት 17 ሺህ ያህል የመሬት መንቀጥቀጥ መፈጠራቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
አገሪቱ ምንም እንኳን ለመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ ባትሆንም በዚህ መልኩ በአጭር ጊዜ በርካታ ክስተት ሲፈጸም ግን ይህ የመጀመሪያው ነው ያለው ዘገባው፤ ከፍተኛው ረቡዕ ዕለት የተከሰተውና በርዕደ መሬት መለኪያ 5.6 የተመዘገበው እንደነበርም አስታውሷል፡፡
በተከታታይ ቀናት ሌሎች የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች በፍጥነት መፈጠራቸውን የጠቆመው ዘገባው፤ ከክስተቶቹ ብዛት አንጻር ያን ያህል የከፋ ጉዳት አለመድረሱንም አክሎ ገልጧል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች ክስተቱ ያልተለመደ መሆኑን ጠቅሰው፣ ሳምንቱን ሙሉ መሬት ከጧት እስከ ማታ ስትንቀጠቀጥ መመልከት ራስን ከተፈጥሮ መከላከል የማይችል ቅንጣት አቅም የለሽ ፍጡር አድርጎ የመቁጠር ስሜትን ይፈጥራል ማለታቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡
Published in
ከአለም ዙሪያ
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል