Sunday, 28 February 2021 00:00

የዕውቁ ድምፃዊ ጥላሁን ገሰሰ 80ኛ ዓመት ልደትና ያረፈበት 12ኛ ዓመት በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች ሊከበር ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የዕውቁና ተወዳጁ ድምፃዊ የክብር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ 80ኛ ዓመት የልደት በዓልና ከሚወደው ሙዚቃና ከሚወደው ህዝብ የተለየበት 12ኛ ዓመት መታሰቢያ በልዩ ልዩ ኪነ- ጥበባዊ መርሃ ግብሮች ሊዘከር እንደሆነ አዘጋጆቹ ገለፁ፡፡ ትላንት የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተብራራው፣ከመርሃ ግብሮቹ መካከል “ቆሜ ልመርቅ ሽ” የተሰኘውን ዘፈኑን ጨምሮ አስር ዘፈን የያዘ አልበም  ምረቃ ፣በስሙ የሚካሄድ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት የእራት ግብዣና ከሁለት ወራት በኋላ በስሙ የሚካሄድ ተዘዋዋሪ የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡
አልበሙ ከያዛቸው አስር ዘፈኖች መካከል ሁለቱ በዩቲዩብ ለህዝብ የሚለቀቁ ሲሆን፣ቀሪዎቹ ደግሞ በኤስ ኤም ኤስና በአውታር በኩል በድረ-ገፅ ለሽያጭ
እንደሚቀርቡና በተለያየ መልኩ የድምፃዊው ልደትና ህልፈቱ ጊዜ እንደሚዘከር አዘጋጆች በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እብራርተዋል፡፡

Read 8218 times