Monday, 01 March 2021 19:46

6ኛው አገራዊ ምርጫ - 2013 "ምርጫው ፍትሃዊ ከሆነ ማሸነፋችን አይቀርም"

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 • ትልቁ አጀንዳችን ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ነው
     • ዎላይታነት ተግባር ነው፤ ዎላይታነት አስተሳሰብ ነው
     • ሌሎች ሃይሎች እንደሚሉን ዘር-ተኮር አይደለንም
     • ተወዳዳሪዎች ላይ የሚፈፀሙ ጫናዎች ያሳስቡናል

          የክልልነት ጥያቄ ከሚነሳባቸው የደቡብ አካባቢ አንዱ የዎላይታ ዞን ነው፡፡ አወዛጋቢ የክልልነት ጥያቄ እየቀረበበት ባለው ዎላይታ ለዘንድሮ ምርጫ የፓርቲዎች አሰላለፍ ምን ይመሰላል? ዋነኛ ተፎካካሪዎች እነማን ናቸው? የምርጫው ዋነኛ አጀንዳ ምንድን ነው? በሚሉና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄንና የዎላይታ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ግንባር የመሰረቱት (የዎላይታ ቱሳ ዲሞክራሲያዊ ግንባር) ሊቀ መንበር ከሆኑት አቶ አማኑኤል ሞጊሶ ጋር
የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ተከታዩን ቆይታ አድርጓል፡፡


          የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) የምርጫ ዝግጅት ምን ይመሰላል? ለምርጫው በከፍተኛ ትኩረት እየቀሰቀስን ነው፡፡ የእጩ ምልመላ እያጠናቀቅን ነው። በዚሁ መሃል ደግሞ በዎላይታ ጠንካራ መሰረት ከነበረው የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎህዴፓ) ጋር ግንባር ፈጥረናል፡፡
የሁለታችንን ለየብቻ መንቀሳቀስ በተመለከተ ግምገማ አድርገን፣ በመካከላችን የመስመርም የአላማም የ ግብም ል ዩነት እንደሌለ ተ ረድተን፣ ለብቻቸው መጓዛቸው አስፈላጊ አይደለም ብለን ተወያይተን ነው ግንባር የፈጠርነው። የሁለቱን ፓርቲዎች ግንባር መፍጠር በጠቅላላ ጉባኤያችን አረጋግጠንም፣ ሰነዱን ለምርጫ ቦርድ አስገብተናል፡፡ የተፈጠረው ግንባር ምን ይባላል? የዎላይታ ቱሳ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ይሰኛል የፈጠርነው ግንባር፡፡ ግንባሩን በሊቀ መንበርነት እንድመራ የተመረጥኩትም እኔ ነኝ፡፡ ይሄ ሃይልን፣ ጉልበትንና ገንዘብን በጋራ አሰባስቦ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ በእጅጉ ያግዘናል፡፡ እኛ ለምርጫው ብቻ አይደለም ግንባሩን የፈጠርነው፤ የህዝቡን አንድነት ለማምጣት ጭምር ዘላቂ ራዕይ አስቀምጠን ነው፡፡ ፓርቲዎቹ በቀጣይ እስከ ውህደት
እንደሚደርሱም አ ቅጣጫ ተ ቀምጧል። የምርጫ ዝግጅታችንም በጋራ ይሆናል፡፡ አሁን ዝግጅታችንን ወደ ማጠናቀቁ ደርሰናል፡፡ የግንባሩ አላማና ግብ ምንድን ነው ? በዝርዝር ያስቀመጣችሁት አላማና ግብ ካለ ቢገልጹልን?
አንደኛ ህዝቡ በተለያየ ደረጃ የጠየቃቸውና እየጠየቃቸው ያሉ የመብትና የእኩልነት ጥያቄዎች አሉ፡፡ ዎላይታ እንደ ብሔር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ፣ ሞራላዊና ታሪካዊ መብቱን ማረጋገጥ አንዱ ግባችን ነው፡፡ ህዝቡ በወከላቸው ልጆች እንዲመራ ማስቻል፣ እውነተኛ ዴሞክራሲን በተግባር ማሳየት ነው አላማችን፡፡ ዎላይታ በጣም የቆየ ታሪክ፣ ስርወ መንግስት፣ አደረጃጀት ያለው ብሔር ነው። አንድን ህዝብ ብሔር ለማለት የሚያስችሉ
አለማቀፍ መስፈርቶችን የሚያሟላ ነው። ከዛሬ 150 አመታት በፊት ስልጣኔ የነበረው ህዝብ ነው። ያንን ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱን መመለስ ነው ግባችን፡፡ በሌላ በኩል፤ የወላይታ ህዝብ የተጋፈጣቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኢ-ፍትሀዊነቶች አሉ። እነዚህን ኢ-ፍትሀዊነቶች መፍታት ሌላኛው ግባችን ነው፡፡ የኛ አላማ በምርጫ የማሸነፍና ያለማሸነፍ ብ ቻ አ ይደለም። የዎላይታ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ መብቱን እንዲለማመድ ማድረግ
ነው፡፡ በዚህ ምርጫ ላይ ስትሳተፉ በምን መርህ ነው? እኛ እንደ መርህ ፍትሀዊነትን ይዘን ነው የምንቀሳቀሰው፡፡ እኛ ዝም ብሎ በዎላይታነት ብቻ ድምፅ እናገኛለን ብለን አይደለም የምንሳተፈው፡፡ ሌሎች ሃይሎች እንደሚሉን ዘር ተኮር አይደለንም፡፡ እኛ ዎላይታ ብለን ስንነሳ ከ ደም ጥ ራት ወ ይም ው ልደት ጋ ር የሚያያዝ አይደለም፡፡ ዎላይታነት ተግባር ነው፡፡ ዎላይታነት አስተሳሰብ ነው፡፡ ስለዚህ እኛ የምንበይነውን የሚያሟላ የትኛውም ዘር ሊሆን ይችላል እሱ ዎላይታ ነው፡፡ ያንን የማያሟላው ደግሞ በ ደም ዎላይታ ነ ኝ ቢ ልም እሱ ዎላይታ አይደለም፡፡ ዎላይታነት በደም የሚወረስ አይደለም። ዎላይታነት በተግባር
ነው የሚገኘው፡፡ ስለዚህ እኛ የምንቆመው ለወላይታነት ነው ስንል፣ በዎላይታነት ውስጥ ላሉ ሁሉ ማለት ነው፡፡ ሁሉንም በእኩል እናገለግላለን። አንዱ ሌላውን አሸማቅቆ የሚገፋበትን ሁኔታ አጥብቀን እንቃወማለን፡፡ መርሀችን ፍትሃዊነት ነው፡፡ በምርጫው ማን ነው የእናንተ ዋነኛ ተፎካካሪያችሁ? እኛ በሃገር ደረጃ ያሉ ሁሉንም ፓርቲዎች ድክመትና ጥንካሬ በሰፊው እየገመገምን ነው። አሁን ባለው ደረጃ የእኛን ግንባር ይገዳደራል ብለን የምናስበው ፓርቲ የለም። ብልጽግና እንደሆነ መጀመሪያውኑ ለህዝቡ ጥያቄ አሻፈረኝ ብሎ ተቀባይነቱን አጥቷል። ኢዜማም ቢሆን ዎላይታ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በትክክል የሚመልስ ስትራቴጂ ሲያስተዋውቅ አላየነውም። ሌሎች ሁለት ፓርቲዎች አሉ፡፡ እነሱም ቢሆኑ ከህዝቡ ራስን በራስ ማስተዳደር ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው አቋሞች ሲያራምዱ አይስተዋሉም። እኛ በቀጥታ የህዝቡን የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ተሸክመን ነው ወደ ምርጫው የምንገባው፡፡ በዚህም ከሌሎቹ የተሻለ ለህዝቡ ፍላጎት የቀረበ እንቅስቃሴ እያደረግን ነው ብለን እናምናለን፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ በፖለቲካ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ዘርፍ ያሉ የዎላይታ ህዝብ ችግሮችን አጥንተን የፖሊሲ አማራጮችን ስናዘጋጅ ነው የቆየነው፡፡ በዎላይታ ምሁራን የተሰናዱ 7 ዋነኛ ፖሊሲዎች አሉን፡፡ በተለይ የወጣቱን ስደትና መፈናቀል የሚያስቆሙ የፖሊሲ አማራጮችን ይዘን ነው የመጣነው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ የዎላይታ ታዳጊ ትምህርቱን
እንኳ በአግባቡ ሳይገፋ በኑሮ ተገፍቶ፣ በአዲስ አበባና ሌሎች ክልሎች ተበታትኖ፣ ለስራ እየተሰደደና ለጉስቁልና እየተዳረገ ነው፡፡ ይሄ መጥፎ ጠባሳ የሚጥል ነው፡፡ ትናንት ደቡብ ላይ ዎላይታ ነበር በዘመናዊ ትምህርት ፈር ቀዳጁ፤ አሁን ግን ይሄ ተለውጧል፡፡ የተማረ ትውልድ እየመከነ ነው፡፡ ተማሪዎች አሁን ላይ ከገጠር ወደ ከተማ እየተሰደዱ ነው፡፡ በአውሮፓና አሜሪካ እንደተበተነው ኢትዮጵያዊ ነው፣ የዎላይታ ታዳጊዎች በየከተማው ተበትነው ያሉት፡፡ ይሄ
ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ እንደ ማህበረሰብም እንደ ሃገርም አደጋ ነው የሚሆነው፡፡ አንድ የሆነ የማህበረሰብ ክፍል ይፈጠራል ማለት ነው። የዜግነት ፖለቲካ የሚያራምዱ አካላት ይሄን እንዴት ነው የሚያስተናግዱት? መጀመሪያ የአካባቢውን ህዝብ ስነ ልቦናና ሞራል መጠበቅ ይቀድማል። አካባቢያዊ ችግሮችን እየፈታን ስንሄድ ነው፣ ዜግነት ብለን አጉልተን ልንንቀሳቀስ የምንችለው፡፡ ይሄ ሁኔታ ውሎ አድሮ አንድ የትውልድ አንጓ ይፈጥራል ማለት ነው፡፡ እኛ ይሄ
የዎላይታ ህዝብ ላይ እንዲያጋጥም አንፈልግም። ስለዚህ ከቀየው ፈልሶ የሄደው ተመልሶ የሚማረው መማር፣ የሚሰራው መስራት አለበት ብለን ነው የተነሳነው፡፡ ለእነዚህ ችግሮች መልስ የሚሰጡ ሰፊ ጊዜ ተወስዶ በምሁራን የተዘጋጁ የፖሊሲ አማራጮች አሉን፡፡ ስለዚህ ምርጫው ፍትሃዊ ከሆነ ማሸነፋችን አይቀርም። ህዝቡ ክልል ልሁን ብሎ ጠይቋል፡፡ በዚህ ጥያቄ የሚደራደር ዎላይታ በአሁኑ ወቅት የለም፡፡ በምርጫው ትልቁ የመፎካከሪያ አጀንዳ
ይሆናል ማለት ነው? በሚገባ! እኛ ራሱ ይሄን አጀንዳ ባንይዝ ህዝቡ ውስጥ ምን እንሰራለን፡፡ ትልቁ አጀንዳችን ራስን በራስ ማስተዳደር ወይም የክልል መዋቅር ጥያቄ ነው፡፡ እኛ የክልል ጥያቄ ስንጠይቅ የመሬት ይገባኛል አይደለም፤ የሞራል የታሪክና የፍትህ ጥያቄ ነው፡፡ ዎላይታ የራሱ የሰለጠነ አስተዳደር
የነበረው ህዝብ ነው፡፡ ዎላይታ ትልቅ ብሔር ነው፤ ክ ልል ለ መሆን ም ንም የ ሚጎደለው ነገር የለም፡፡ የመዋቅር ችግሩን አስተካክሎ፣ የተወላጆቹን ችግር የመፍታት አላማ ነው ያለን። እንዴት? ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አስተዳደር ክልላዊ ነው፡፡ ግንኙነቱ ክልል ከክልል እንጂ ዞን ከክልል አይደለም፡፡ በዚሁ የመዋቅር ችግር የተነሳ ዎላይታ ባለቤት አልባ ነው የሆነው፡፡ ዎላይታ በአዲስ አበባ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ ሌሎች ክልሎች በሙሉ ተዟዙሮ የሚሰራ ነው፡፡ ልክ እንደ አማራ ጉራጌ ተበታትኖ ያለ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ኦሮሚያ ላይ ዎላይታ ችግር ቢገጥመው፣ አሁን ባለው መዋቅር መደራደር እንኳ አይችልም፡፡
ምክንያቱም ዞን ከክልል ጋር በቀጥታ መነጋገር አይችልም፡፡ ስለዚህ መዋቅሩ የዎላይታን መብት ለማስከበር አቅም አይሰጥም፡፡ ክልል ከሆነ ግን ከሌሎች ክልሎች ጋር የመደራደርና የመወያየት አቅም እናገኛለን ምን ያህል እጩዎች ነው ያዘጋጃችሁት?
ለፌደራል ዞኑ ያለው ኮታ 13 ነው። ለደቡብ ክልል ደግሞ 39 ነው፡፡ እኛ በሁሉም ላይ እጩዎች አዘጋጅተናል፡፡ በርካታ ምሁራንን ነው በእጩነት እየመረጥን ያለነው፡፡ እጩዎቻችንንም በተለያዩ አካባቢዎች እየገመገምን ነው፡፡ ዎላይታ አሁንም ዞን ነው፡፡ እናንተ በምርጫው ካሸነፋችሁ ለደቡብ ክልል 39 ወንበር መያዝና 13 የፓርላማ ወንበር መቆጣጠር እንዲሁም ዞ ኑን ማ ስተዳደር ሊ ሆን ይ ችላል። ይሄን እድል ብታገኙ በምን አይነት መንገድ ነው የዎላይታ ጥያቄዎችን ምላሽ ልትሰጡ የምትችሉት?
አንደኛ የሰላማዊ ትግል አማራጮችን በሙሉ እንጠቀማለን፡፡ እስካሁንም መንግስት የክልልነት ጥያቄውን ያልፈታበትን ምክንያት ማንም አያውቀውም፡፡ መንግስት ጥያቄውን ባለቤት አልባ አድርጎ ለማምታታትም እየተሞከረ ነው፡፡ ይሄ ባለቤት አልባ ተደርጎ ለማሳየት የተሞከረው የክልልነት ጉዳይ ባለቤት እንዳለው በምርጫው ይረጋገጣል። አሁን ሾላ በድፍኑ ነው ያለነው። ህዝበ ውሳኔውን ሲያሳውቅ ሁሉም ግልጽ ይሆናል፡፡ እኛ እስከ መጨረሻው የምንታገልለት አላማችን ስለሆነ የሰላማዊ ትግል አማራጮችን በሙሉ እንጠቀማለን፡፡
ከምርጫው ጋር በተገናኘ ተስፋና ስጋታችሁ ምንድን ነው?
ከስጋቱ ስንጀምር ምርጫው ይጭበረበራል የሚል ነው ስጋታችን። ያለፉት ምርጫዎች በዚህ መልኩ ያለፉ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ሌላው ተወዳዳሪዎች ላይ የሚፈፀሙ ጫናዎችና ወከባዎች ያሳስቡናል፡፡ ተስፋችን ደግሞ የህዝብ ጥያቄ ነው፡፡ ህዝባችን ከጎናችን መሆኑ ነው ተስፋችንን ከፍ የሚያደርገው፡፡



Read 1388 times