Sunday, 28 February 2021 00:00

አማራ ባንክ (አባ) ሊመሰረት ነው

Written by 
Rate this item
(2 votes)

    ከአንድ መቶ ሰማኒያ ስምንት ሺ በላይ ባለ አክሲዮኖችን ቤተሰብ ያደረገ ባንክ ነው፡፡ ከስምንት ቢሊዮን ብር በላይ የተመዘገበና ስድስት ቢለዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ወደ ምስረታ እየገሰገሰ የሚገኘው አማራ ባንክ፤ በነገው ዕለት ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የባንክ አደራጆችና ባለ
አክሲዮኖች በተገኙበት የመስራች ጠቅላላ ጉባኤ ያካሂዳሉ፤ ምስረታውንም ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የአማራ ባንክ 30 በመቶ አክሲዮን የሸጠ
ሲሆን ባንኩ ስራ ሲጀምር በመላው የሀገራችን አካባቢዎች ቅርንጫፎችን በመክፈት አዳዲስ አገልገሎቶችን ያስተዋውቃል ተብሏል፡፡ በተያያዘ ዜና፤ አማራ ኢንሸራንስ አክሲዮን ማህበር (አ.ማ) ለመመስረት በዝግጅት ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡


Read 4902 times