Print this page
Tuesday, 23 February 2021 00:00

ጃፓናውያን በስራ፣ ደቡብ አፍሪካውያን በእንቅልፍ ብዙ ጊዜ ያሳልፋሉ

Written by 
Rate this item
(5 votes)

  ኦርጋናይዜሽን ፎር ኢኮኖሚክ ኮኦፕሬሽን የተባለው ተቋም፣ በ33 የአለማችን አገራት የሚኖሩ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 64 አመት የሚገኙ ሰዎች፣ ጊዜያቸውን እንዴት እንደሚጠቀሙ ለማወቅ በሰራው ጥናት፤ ጃፓናውያን በስራ፣ ደቡብ አፍሪካውያን ደግሞ በእንቅልፍ ከሁሉም አገራት የበለጠ ጊዜ እንደሚያጠፉ ማረጋገጡን አስታውቋል።
ጃፓናውያን ክፍያ በሚያገኙበት መደበኛ ስራ ላይ በቀን በአማካይ 5.5 ሰዓታትን እንደሚያጠፉ የጠቆመው የድርጅቱ ጥናት፤ ደቡብ አፍሪካውያን በአንጻሩ 9 ሰዓታትን ያህል በእንቅልፍ እንደሚያጠፉ አመልክቷል።
በተለያዩ የመዝናኛ መንገዶች በየቀኑ ከፍተኛ ጊዜ በማጥፋት ቀዳሚነቱን የያዙት የኖርዌይ ዜጎች ሲሆኑ፣ በአገሪቱ አንድ ሰው በአማካይ በቀን 6.5 ሰዓታትን እንደሚያጠፋ የጠቆመው መረጃው፤ምግብ በመመገብ ፈረንሳውያን በቀን 2 ሰዓታትን  በማጥፋት፣ አሜሪካውያን ደግሞ ቴሌቪዥን በመመልከትና ሬዲዮ በማዳመጥ በአማካይ 2.5 ሰዓታትን በማጥፋት በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸውን አስታውቋል፡፡
በሁሉም አገራት ክፍያ በማያገኙበት የቤተሰብ እንክብካቤ ስራ ላይ ሴቶች ከወንዶች ጋር ሲነጻጸር በ3 እጥፍ ያህል የሚበልጥ ጊዜ እንደሚያጠፉ የተነገረ ሲሆን፣ ሴቶች በየአመቱ በመሰል ስራዎች ላይ በአማካይ 1.1 ትሪሊዮን ያህል ሰዓታትን እንደሚያጠፉም ለማወቅ ተችሏል፡፡


Read 11752 times
Administrator

Latest from Administrator