Sunday, 07 February 2021 00:00

“ከአገሬ ሰማይ ስር” የጥበብ ምሽት - በብሔራዊ ቴአትር “እስከ መቼ” የኪነጥበብ ምሽት - በኢትዮጵያ ሆቴል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  በጉዞ ሚዲያና ማስታወቂያ የሚዘጋጀው “ብራና” የኪነ ጥበብ ምሽት፣ ከነገ በስቲያ  ሰኞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ “እስከ መቼ” በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ በዕለቱ ዲስኩር፣ ወግ፣ ግጥምና ሙዚቃ  የሚቀርብ ሲሆን ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ፣ አቶ ኦባንግ፣ አርቲስት አስቴር በዳኔ፣ አርቲስት ደሳለኝ ሀይሉ ዲስኩር፣ ገጣሚያኑ ኤፍሬም ስዩምና አንዷለም አባተ (የአፀደ ልጅ) ግጥም፣ ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ወግ እንደሚያቀርቡና ድምጻዊ ካሳሁን እሸቱ ከሻሎም አቢሲኒያ የባህል ቡድን ጋር እንደሚያቀነቅን  ተጠቁሟል፡፡ መድረኩ በጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ የሚመራ ሲሆን የመግቢያ ዋጋ 100 ብር ነው ተብሏል፡፡ ትኬቶቹ በጃፋር፣አይናለምና ዮናስ መጽሀፍት መደብሮችና በኢትዮጵያ ሆቴል እንደሚገኙም ታውቋል፡፡
በተመሳሳይ ዜና፤ በሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት በየወሩ የሚዘጋጀው ጥበባዊ ምሽት የፊታችን ሰኞ ከ11፡00 ጀምሮ “ከአገሬ ሰማይ ስር” በሚል ርዕስ በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል። በዕለቱም ዲስኩር፣ ወግና ሙዚቃ የሚቀርቡ ሲሆን ወዳጄነህ ማህረነ (ዶ/ር)፣ ሲሳይ መንግስቴ (ዶ/ር)፣ ደራሲ ሕይወት እምሻው፣ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር)፣ ጋዜጠኛ ጌጡ ሰምሀር ተክኢ (ዶ/ር)፣ ገጣሚ ሰይፉ ወርቁ፣ ባንቻየሁ አሰፋና መአዛ ፋንታዬ የጥበብ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል። አድዋ ሙሉ ባንድ የኪነጥበብ ምሽቱን  በሙዚቃ ያደምቀዋል ተብሏል፡፡ የመግቢያ ዋጋው 100 ብር ሲሆን ትኬቶቹ በጃዕፋር፣ በዮናስ፣ በዘውዱ እና በዕውቀት በር መፃሕፍት መደብሮች እንደሚገኙም ታውቋል፡፡

Read 11020 times