Saturday, 30 January 2021 16:29

ዳሞታ ባንክ ሊመሰረት ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

ከ370 ሚ. ብር ካፒታል ማስፈረም ችሏል ለኪነ ጥበብ-ሥራዎች ብድር ይፈቅዳል
                   
               በባንክ የሙያ ዘርፍ ከብሔራዊ ባንክ  ጀምሮ ዓለም አቀፍ እውቀት ልምድ ባካበቱ አደራጆች የተቋቋመው ዳሞታ ባንክ ሊመሰረት ነው። ባንኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ 370 ሚ. ብር የተፈረመና  ከግማሽ በላይ የተከፈለ ካፒታል መሰብሰቡን ባለፈው ረብዕ ረፋድ ላይ አደራጆቹ በካፒታል ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
ባንኩ ቴክኖሎጂን መሰረት አድርጎ ነገር ግን እስከ ታች የማህበረሰቡ ክፍል ወርዶ ለመስራትና በአገራችን ያሉ በጣት የሚቆጠሩ ባንኮች ያልዳሰሷቸውን ዘርፎች ለመድረስ አልሞ መቋቋሙን የመስራቾች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኤሊያስ ቡሃይ ተናግረዋል። ዳሞታ፤ ተማሪዎችን፣ አርብቶ አደሮችን፣ አነስተኛና ጥቃቅን ድርጅቶችን ለመድረስ ከማቀዱም በላይ ሀሳብን ፋይናንስ የማድረግ (Idea Financing) ላይም እንደሚሰራ ገልጿል።
አዋጭ ሀሳብ ይዘው ገንዘብ በማጣት ለተቀመጡ ባለተሰጥኦ ስራ ፈጣሪዎች ባንኩ የፕሮጀክት አማካሪ ቢሮ ከፍቶ፣ ሀሳባቸው እንዲያዳብርና በጥናትና ምርምር እንዲደግፋቸው በማድረግ ጭምር ለስኬት እንደሚበቃም አስታውቋል።
የባንኩ የአንድ አክሲዮን ትንሹ ዋጋ 1  ሺህ ብር ሲሆን፣ አንድ ሰው መግዛት የሚችለው ትንሹ 50 ሺህ ብር፣ ትልቁ ደግሞ 100 ሚ. ብር መሆኑንም  አደራጆቹ ገልጸዋል።
አደራጆቹ አክለውም፤ ኪነ-ጥበብ ለአንድ ሀገር ትልቅ ዋጋ ያለው በመሆኑ፣ ኪ-ጥበብ ዘርፉን እንደሚደግፉና  ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ለሚያሰሯቸው የኪነ-ጥበብ ስራዎች ብድር እንደሚፈቅዱም ተናግረዋል።


Read 2104 times