Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 11 August 2012 12:32

ዓለማየሁ ገላጋይ “የፍልስፍና አፅናፍ”ን ለገበያ አቀረበ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ጋዜጠኛ፣ ደራሲና ሃያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ “የፍልስፍና አፅናፍ” የተሰኘ በፍልስፍና ሃሳቦች ላይ የሚያጠነጥን መፅሃፍ በመተርጐም ሰሞኑን ለንባብ አብቅቷል፡፡መፅሃፉ የተተረጐመው ከአሜሪካዊው የ20ኛው ክ/ዘመን ፈላስፋ ከዶ/ር ሞርቲመር ጄሮም አድለር “Great Ideas From The Great Books” የተሰኘ የፍልስፍና መፅሃፋቸው ላይ እንደሆነ ተገልጿል - በመፅሃፉ መግቢያ፡፡  መፅሃፉ በአምስት ክፍሎች የተዘጋጀ ሲሆን ፍልስፍና፣ ህይወት፣ ሃይማኖት፣ ፍቅርና ፖለቲካ የሚሉ ርእሶች ተሰጥቶታል፡፡በእያንዳንዱ ርእሰ ጉዳዮች ለቀረቡ የረቂቅ ሃሳብ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት የሚያብራራው መፅሃፉ፤ የህይወት ዓላማ ምንድነው? የፖለቲካ መሪዎች ፍልስፍና፣ አገር ወዳድነትና ዓለም አቀፋዊነት፣ ስንት አይነት ፍቅር አለ? ወዘተ… በሚሉ ፍልስፍናዊ ሃሳቦች ዙርያ ትንተናዎችን ያስቀምጣል፡፡

ተርጓሚው ዓለማየሁ ገላጋይ እነዚህን የፍልስፍና ርእሰ ጉዳዮች በ”ፍትህ” ጋዜጣ ላይ በመተርጐም ሲያቀርብ እንደቆየ በመፅሃፉ መግቢያ የጠቆመ ሲሆን በ175 ገፆች የተቀነበበው መፅሃፉ በ30 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ዓለማየሁ ገላጋይ ባለፈው ሳምንት ለንባብ የቀረበውን “ኩርቢት” የተሰኘ የአጭር ልብወለድ መድበል ጨምሮ የአምስት መፃህፍት ደራሲና ተርጓሚ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

Read 3392 times Last modified on Saturday, 11 August 2012 12:37