Saturday, 23 January 2021 11:59

ባለፉት ስድስት ወራት ወርቅ በኤክስፖርት ገቢ ይመራል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

       ባለፉት ስድስት ወራት የኤክስፖርት ንግድ በ335 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ወርቅ የመሪነቱን ድርሻ የያዘ ሲሆን ቡና በ304 ሚሊዮን ዶላር በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ የወርቅ ዓመታዊ ገቢ ከዓመት ዓመት እያሽቆለቀለ ከ40 ሚሊዮን ዶላር በታች ወርዶ ነበር፡፡  
አበባ በ213 ሚሊዮን ዶላር፣ ጫት በ187 ሚሊዮን ዶላር፣ የቅባት እህሎች በ150 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ የጥራጥሬ ሰብሎች፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዲሁም ኤሌክትሪክ ከስድስተኛ እስከ ስምንተኛ ያለውን ደረጃ መያዛቸው ተጠቁሟል፡፡  ምግብና መጠጥ፣ የስጋ ወተትና ኢንዱስትሪ ዘርፍ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የቁም እንስሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም ኤሌክትሮኒክስ እንደ የቅደም ተከተላቸው ያለውን ደረጃ መያዛቸውም ታውቋል፡፡


Read 2104 times