Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 11 August 2012 12:09

“ሕይወት በመንግስቱ ቤተመንግስት” ዛሬ ለንባብ ይበቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“ነጭ ለባሽ” ዛሬ ይመረቃል   “አስኳል” በድጋሚ ታተመ

ያለፈው መንግስት ልዩ ኃይል አባል በነበሩት ወንድሙ ወልደ ሥላሴ የተዘጋጀው “ሕይወት በመንግስቱ ቤተመንግስት” መጽሐፍ ለሕትመት በቃ፡፡ ቅፅ  መጽሐፉ ዛሬ ከማተሚያ በመውጣት ለንባብ እንደሚበቃ አዘጋጁ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ መጽሐፉ ከያዛቸው መረጃዎች መካከል የንጉሡ ቀለበት ምስጢር”፣ “የተገረፈው የሲአይኤ አባልና ቀኛዝማች አሰጋኸኝ አርአያ”፣ “የተሸላለሙ አብዮተኞች” እና “የፈረንሳይ አቦ ቤተክርስትያን ጭፍጨፋ” ይገኙበታል፡፡ 156 ገፆች ያሉት መጽሐፍ በሰላሳ ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ በመላኩ ደምለው የተዘጋጀው “ነጭ ለባሽ” ረዥም ልቦለድ ዛሬ ይመረቃል፡፡ ከጧቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ሆቴል የሚመረቀው መጽሐፍ፤ ለደራሲው ሦስተኛ የታተመ ሥራቸው ነው፡፡ 318 ገፆች ያሉት መጽሐፍ ገበያ ላይ በ45 ብር ይገኛል፡፡ በሌላም በኩል የአሜሪካዊው ልብሰቀላ ድርሰት ፀሐፊ ሲድኒ ሸልደን Master of the Game በ1981 ዓ.ም በፋንታሁን ኃይሌ ዮሴፍ “አስኳል” ተብሎ መተርጎሙ የሚታወስ ሲሆን ከ23 ዓመት በኋላ በድጋሚ ታትሞ ለንባብ በቃ፡፡ 252 ገፆች ያሉት መጽሐፍ በ38 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

 

 

 

 

Read 1362 times Last modified on Saturday, 11 August 2012 12:17