Saturday, 23 January 2021 11:02

የአራት ክልሎች የም/ቤት መቀመጫ ብዛት ለውጥ ተቀባይነት አላገኘም

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

     የአዲስ አበባ አስተዳደርን ጨምሮ አራት ክልሎች የምርጫ ክልል (የመቀመጫ ብዛት) ለውጥ ጥያቄ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቢያቀርቡም፣ ቦርዱ ጊዜው ያለፈበት ጥያቄ ነው ሲል አልተቀበለውም።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የአስተዳደሩን የምርጫ ክልል ወይም የመቀመጫ ብዛት ከፍ ለማድረግ ማመልከቻ ማስገባቱን፤ እንዲሁም የአፋር ብሔራዊ ክልል፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልላዊ መንግስትና የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ተመሳሳይ ጥያቄ ማቅረባቸው ተመልክቷል።
በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ-ምግባር አዋጅ መሰረት እንዲህ ያሉ ጥያቄዎች መቅረብ ያለባቸው ለምርጫ እጩዎችን የማቅረብ ሂደት ከመጀመሩ 6 ወራት አስቀድሞ መሆኑን የጠቆመው ምርጫ ቦርድ፤ በዚህ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ሆነ የክልሎች ጥያቄ ህጉን ተከትሎና ጊዜውን ጠብቆ የቀረበ አይደለም ብሏል። በዚህ መሰረት ቀጣዩ ምርጫ የከተማ አስተዳደሩም ሆነ ክልሎቹ በነበራቸው የምርጫ ክልል (መቀመጫ ብዛት) መሰረት ይካሄዳል ብሏል። የአዲስ አበባ አስተዳደርና ክልሎቹ ያቀረቡት ጥያቄ፣ በየአስተዳደራቸው ም/ቤት አባላት ብዛት ላይ ለውጥ የሚያመጣ ጥያቄ ነበር።

Read 12282 times