Monday, 18 January 2021 00:00

የበቃሉ ሙሉ “እኔና ክርስቶስ” የግጥም መድበል ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 “ብራና እና ወናፍ” እና የማያልቅ አዲስ ልብስ” በተሰኙ በ2008 እና 2010 ዓ.ም በታተሙ የግጥም መድበሎቹ የምናውቀው ገጣሚ በቃሉ  ሙሉ ሶስተኛ ስራ የሆነው “እኔ እና ክርስቶስ” የተሰኘው የግጥም መድበል ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡
መድበሉ 41  ያህል ግጥሞችን በውስጡ የያዘ ሲሆን፣ ግጥሞቹ ስለ ሀገር ምንነት፣ ስለተፈጥሮና የሰው ልጅ ህይወት ምርምር፣ሀይማኖታዊ ፍልስፍናዎች፣ በመኖር የታዩ ሁኔታዎችን የመጠየቅ ማህበረሰባዊና ግላዊ የህይወት ሙግቶችና በርካታ ፍልስፍናዎች እንደተንጸባረቁበት ገጣሚው ገልጿል፡፡ በ100 ገፅ የተቀነበበው መፅሀፉ በ81 ብር ከ50 ሳንቲምና በ25 ዶላር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል፡፡
ገጣሚው በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ምሽቶች ላይ በሚያቀርባቸው ፍልስፍናዊ ግጥሞቹ የሚታወቅ ሲሆን በ2008 እና በ2010 ዓ.ም ካሳተማቸው የግጥም መድበሎቹ በተጨማሪ በ2012 ዓ.ም በታተመውና 17 ደራሲያን በተሳተፉበት “አቦል” መፅሀፍ ላይ ስራዎቹ ታትመው ለንባብ መብቃታቸው አይዘነጋም፡፡

Read 9229 times