Monday, 18 January 2021 00:00

“ትናንት በንጉስ አንደበት” ለአንባቢያን ቀርቧል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   በደራሲና የቀድሞ ጦር አባል ዶ/ር ለማ በላይነህ የተደረሰው “ትናንት በንጉሱ አንደበት”  የተሰኘው ልብ ወለድ መፅሀፍ ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡
በ314 ገፆች ተቀንብቦ በፋር ኢስት ትሬዲንግ ታትሞ ለንባብ የበቃው መፅሐፉ፤ ለሀገር ውስጥ አንባቢያን በ150 ብር ለውጭ ሃገር በ20 ዶላር ይሸጣል፡፡ ደራሲው ዶ/ር ለማ በላይነህ ካሳዬ፣ ተወልደው ያደጉት አዲስ አበባ አባ ኮራን ሰፈር ሲሆን የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የቀድሞ ወሰን ሰገድ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በቀድሞ ልዑል መኮንን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡ በእድገት በህብረት ዛቻ በኋላ በፈረንጆቹ 10976 የቀድሞ አየር ሃይልን ተቀላቅለው እስከ ሻምበል ማዕረግ ደርሰዋል፡፡
በዚህ ጊዜ ውስጥ በአየር ሃይል “ተነሳ ተራመድ”ና የቀድሞ የጦር ሃይሎች ልሳን በነበረው ካምፕ ታጠቅ ጋዜጣና መፅሄት አዘጋጅና የሜካፕ ኤዲተር በመሆን አገልግለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በህዝብ አስተዳደርና ማኔጅመንት የባችለር ድግሪ እንዲሁም በቀድሞ ሶቪየት ህብረት በኢኮኖሚክስ የማስተርስና ዶክትሬት ድግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት የሆኑት ውስጥ ሲሆን ባለትዳርና የአንድ ሴት ልጅ አባት ናቸው፡፡
ይሄ “ትናንት በንጉሱ አንደበት” በሚል ከታተመው መጽሐፋቸው በፊት “ምስክር የጠፋው ትውልድ ዕድምተኛ” በሚል ርዕስ መጽሀፍ አሳትመው ለንባብ አብቅተዋል፡፡ ደራሲው አሁንም የቀድሞ አየር ሃይል አለም ዓቀፍ ህብረት በየአመቱ በሚያወጣው “ተነስ ተራመድ” መፅሄት በትርፍ ጊዜያቸው በዋና አዘጋጅነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

Read 2471 times