Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 11 August 2012 11:59

የአሚር ካሃን ቶክ ሾው ተደነቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በቦሊውዱ ምርጥ ተዋናይ አሚር ካሃን የሚዘጋጀውና በህንድ ማህበራዊ ችግሮች ዙሪያ መፍትሄ በማፈላለግ የሚሰራው ቶክ ሾው ከፍተኛ አድናቆት ማትረፉን ዘ ሂንዱስታን ታይምስ ዘገበ፡፡ ‹ሳታያሜቭ ጃያቴ› የሚል መጠርያ ያለው ይኸው ቶክ ሾው፤ እውነት ብቻ ነፃ ያወጣል በሚል መርህ የሚቀርብ ነው፡፡ ስታር ኢንድያ በተባለ የቴሌቭዥን ጣቢያ ላለፉት ሶስት ወራት ሲቀርብ የቆየው ፕሮግራሙ፤ ባለፉት 20 ዓመታት በምርጥ ትወናው ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኘው አሚር ካሃን ለመጀመርያ ጊዜ በቴሌቭዥን መስራት የጀመረበት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ አሚር የቶክ ሾውን የመጀመርያ አመት ባለፈው ሳምንት ሲያጠናቅቅ ለሚቀጥሉት አምስት አመታት ስራውን አሳድጎ የመቀጠል ፍላጎት እንዳለው ተናግሯል፡፡ ተዋናዩ በበርካታ የፊልም ስራዎች ላይ በትወና እና በፕሮዲውሰርነት መሳተፉ ከፍተኛ የስራ ውጥረት ውስጥ ሊከተው ይችላል ተብሏል፡፡ ቶክ ሾው በዋናነት በስታር ኢንድያ ብሮድካስት ኩባንያ የሚሰራጭ ቢሆንም በ10 የተለያዩ ጣቢያዎች በመተላለፍ በ21 ሚሊዮን ህንዳውያን መኖርያ ቤት የገባ ፕሮግራም ሲሆን በሰባት ቋንቋዎች  ይቀርባል፡፡

የ47 ዓመቱ አሚር ካሃን፤ ይህን ቶክ ሾው ለማዘጋጀት በኩባንያው በኩል 630ሺ ዶላር በጀት እንደመደበ ታውቋል፡፡ በቃለምልልሶች እና በቀጥታ በሚሰራጩ የዘገባ ሽፋኖች የሚሰራው ቶክ ሾው፤ በህንድ የጤና፤ የመሰረተ ልማት እና የማህበረሰብ ችግሮች እና አጀንዳዎች ላይ በመስራት በአጭር ጊዜ ባበረከተው አስተዋፅኦ ስኬትን ተቀዳጅቷል፡፡ አሚር ካሃን በቶክ ሾው ላይ በነበረው አቀራረብ የህንድ ኦፕራ ዊንፍሬይ፤ ቦኖ እና ጆርጅ ኩሉኒ በሚል ተወድሷል፡፡ ሂንዱስታን ታይምስ ጋዜጣ ላይ በአምደኛነት የሚሳተፈው አሚር ካሃን፤ ከፊልም ስራ ወጥቶ በቶክ ሾው ፕሮግራም በመስራት ከፍተኛ ክብር እና አድናቆት እንዳተረፈም ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

Read 1689 times Last modified on Saturday, 11 August 2012 12:08