Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 11 August 2012 11:56

150 ሚ.ዶላር የሚያወጣ የዳቬንቺ ስእል ተገኘ

Written by 
Rate this item
(5 votes)

ከ500 ዓመታት በፊት የተሰራ የሊዮናርዶ ዳቬንቺ የስእል ስራ በአንድ የስኮትላንድ የገበሬ ቤተሰብ መኖርያ ቤት ውስጥ መገኘቱን ዘ ሃፊንግተን ፖስት አስታወቀ፡፡ ዳቬንቺ  በዚሁ የስእል ስራው ማርያም እና እየሱስን እንደሳለ የሚገልፁ መረጃዎች ቢኖሩም አንዳንድ ባለሙያዎች ስእሉ ማርያም መግደላዊትና ልጇን የሚያሳይ ነው እያሉ ናቸው፡፡ ዘ ሃፊንግተን ፖስት ዴይሊ ሜል ይፋ ያደረገውን መረጃ በመጥቀስ በሰራው ትንተና ስእሉ የዳቬንቺ መሆኑ ከተረጋገጠ እስከ 150 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ሊያወጣ ይችላል ብሏል፡፡

ስኮትላንዳዊያኑ ገበሬዎች ይህን ስእል በ1960ዎቹ በስጦታ እንዳገኙ ተናግረዋል ያለው ዘገባው፤ሊዮናርዶ ዳቬንቺ ስእሉን በ17ኛው ክፍለዘመን ላይ የካቶሊክ መሪ ለነበሩት ፖፕ ፖል 5ኛ የሰራው እንደነበር ገልጿል፡፡ ስእሉ በሊዮናርዶ ዳቬንቺ የተሰራ ኦርጅናሌ ቅብ መሆኑን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ባለሙያዎች ጥናት ማድረግ እንደጀመሩም ታውቋል፡፡

 

 

 

Read 5249 times Last modified on Saturday, 11 August 2012 11:59